በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ በዛሬው ዕለት “በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፥ በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ ጢም አብቅሎ የተወለደ ሕፃን ተገኘ” በሚል ርዕስ በሰፊው እየተዘዋወረ የሚገኝ ምስል WT Media በጥሞና ተመልክቷል።
በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ይህንን መረጃ እንደ እውነት በመውሰድ በርካታ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦችና ገፆች በስፋት ሲያጋሩት ተስተውሏል።

WT Media ይህንን ጉዳይ በማጣሪያ ዜደዎች፣ ከሳይንሳዊ እውነታና ከምስሉ አመጣጥ አንጻር ባደረገው ማጣራት የሚከተሉትን እውነታዎች አረጋግጧል።
- አዲስ የተወለደ ሕፃን በሰውነት አወቃቀሩም ሆነ በባዮሎጂያዊ ተፈጥሮው እንደዚህ ዓይነት ሙሉና ጥቅጥቅ ያለ የጎልማሳ ጢም ይዞ መወለድ አይችልም። ይህ ተፈጥሯዊ ዕድገት አይደለም።
2. የሚታየው ምስል ከዚህ ቀደም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች (ናይጄሪያ፣ ሕንድ እና ሌሎች ሀገራት) በተለያዩ ወቅቶች ሲሰራጭ የቆየ የቆየ የፈጠራ ወሬ (Hoax) ነው። ምስሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ (AI) ወይም በፎቶሾፕ የተፈጠረ መሆኑ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የእውነታ ማጣሪያ ተቋማት ቀደም ሲል የተረጋገጠ ነው።
3. በአሁኑ ወቅት ምስሉ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ሕዝብን ለማደናገርና የሰዎችን ስሜት ለመሳብ የተደረገ ሙከራ ነው።
WT Media ሕብረተሰቡ እንደዚህ ዓይነት ያልተረጋገጡ፣ አጠራጣሪ እና የሰዎችን ስሜት ለመበዝበዝ የሚለቀቁ ምስሎችን ወይም መረጃዎችን ከመጋራቱ በፊት በጥንቃቄ እንዲያጣራ በጥብቅ ያሳስባል።
ማንኛውንም መረጃ ያለማጣራት ማጋራት የሐሰት ወሬዎች እንዲስፋፉና እንዲደጋገሙ መነሻ ይሆናል።
የተረጋገጠ መረጃን ብቻ እናጋራ፤ ከሐሰተኛ መረጃዎች እንጠበቅ!