GridArt_20260724_172632341

የ5 እና 7 ዓመት ሕፃናትን በማታለል ግብረ-ሥጋ ድፍረት የፈጸመው ጥበቃ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ተገልጿል።

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ ሶዶ በር ቀበሌ የንጋት ትምህርት ቤት ጥበቃ በመሆን የሚሠራው ታዲዎስ ሞታ የተባለ ግለሰብ፣ የ5 እና የ7 ዓመት ሕፃናት ላይ የግብረ-ሥጋ ድፍረት በመፈጸሙ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት እንደተፈረደበት የቦዲቲ ከተማ ኮሚኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።

​ግለሰቡ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ሕፃናቱን “ዥዋዢዌ ትጫወታላችሁ” ብሎ በማታለል በሚሠራበት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ወደሚገኝ ማደሪያ ክፍል በማስገባት ወንጀሉን መፈጸሙን ፖሊስ ባሰባሰበው ማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል።

​ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የቦዲቲ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተከሳሹ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 60/ሀ እና 627/1 መሠረት ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን አረጋግጧል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹንና መሰል ወንጀል ፈጻሚዎችን ያስተምራል በሚል የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፎበታል።

WT Media የሕፃናትን ደህንነት የሚነኩ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሆኑ መሰል ጉዳዮችን መረጃዎችን ይዞ መውጣቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።