GridArt_20260727_184539216

የ7ኛው አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ አስፈፃሚዎች የሥራና የትርፍ ሰዓት ክፍያ እስከ አሁን ባለመከፈሉ ተቃውሞ መግጠሙ ተገልጿል።

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም ባካሄደው 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ክፍያ እስከ አሁን ባለመክፈሉ በሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መቀስቀሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

​ምርጫ ቦርድ የገባውን ውል በመጣስ እስካሁን ካልከፈላቸው ክፍያዎች መካከል ​የ60% ቀሪ ክፍያ፣ ​የሥልጠና ጊዜ ክፍያ እና ​በምርጫው ዕለት እስከ ሌሊቱ 6:00 ሰዓት ድረስ ለተሰራበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ የሚገኙበት መሆኑንም ተበዳዮች ቅሬታ አቅርበዋል።

ቦርዱ እነዚህን ክፍያዎች ምርጫው ከተጠናቀቀበት ከግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በውሉ መሠረት እከፍላለሁ ብሎ እንደነበር አስረድተዋል።

​ይሁን እንጂ እስከ ዛሬው ዕለት ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተገባው ቃል ባለመጠበቁ እና አበልና ደመወዛቸው ባለመከፈሉ የምርጫ አስፈፃሚዎቹ ለከፍተኛ እንግልትና ምሬት መዳረጋቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

አስፈፃሚዎቹ በምርጫው ወቅት ሌሊት ሳይሉ ላባቸውን አፍስሰው ለሀገር አቀፍ ሂደት መሳካት አስተዋጽኦ አድርገው ሳለ የተገባላቸውን ውል አክብሮ ክፍያቸውን መክፈት ተገቢ ሆኖ ሳለ ቦርዱ ዝምታን መምረጡ አግባብ እንዳልሆነ አስረድተዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ምርጫ ቦርድ የሰጠው ምላሽ የለም።

​WT Media የምርጫ አስፈፃሚዎችን ፍትሃዊ ጥያቄዎች እና የኪን ማኅበረሰብ ድምጾች አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዚህ የዘገየ ክፍያ እና ለተፈጠረው ቅሬታ የሚሰጠውን ምላሽ የሚከታተል ይሆናል።