GridArt_20260915_215009904

​በማህበረሰብ አገልግሎት እና በሰብአዊ ስራ ዙሪያ የህይወት ዘመን ውድ ዋጋ እየከፈሉ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ብርሃን ለዓለም እየታዩ ነው። ከዚህ አንፃር፣ በ “AidEx Humanitarian Hero of the Year Award” በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተመረጡ 7 የሰብአዊ መሪዎች መካከል አንዱ በመሆን የኢትዮጵያን ስም ከፍ ያደረጉት ዶ/ር ልሳነወርቅ ሆንሴቦ ግንባር ቀደም ናቸው።

​ይህ የዓለም አቀፍ እውቅና የዘፈቀደ አይደለም፤ ይልቁንም በዎላይታ ዞን በአባላ አባያ ወረዳ ጠቅላላ ሐኪም በመሆን ከጀመሩት የሙያ አገልግሎት ጀምሮ ማህበረሰባቸውን በቅንነት ለማገልገል የገቡት ጽኑ ቃል ፍሬ ነው። ዶ/ር ልሳነወርቅ “ሪዲዮ ኢትዮጵያ” (Ridio Ethiopia) የተሰኘውን በጎ አድራጎት ድርጅት ሲመሰርቱ ከራሳቸው የህይወት ገጠመኝ በመነሳት ነው።

እንደ መረጃው ከሆነ በአንድ ወቅት ወላጅ እናታቸው በማህበረሰብ ደረጃ መሰረታዊ የጤና እና የድጋፍ አገልግሎት በማጣታቸው የደረሰባቸውን እንግልት እና ህመም በቅርብ በመመልከታቸው አሁንም በዚሁ ሰቆቃ ውስጥ ላሉ ወገኖች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በመነሳሳት የተመሰረተ ድርጅት ነው።

​ድርጅቱ በ2020 በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ስራውን አሀዱ ብሎ ሲጀምር የነበረው ራዕይ ዛሬ ላይ ትልቅ እመርታ አሳይቷል። በ16 የተለያዩ ዘርፎች የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በማከናወን ከ63,000 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።

​በጎ ፈቃድ ያነሳሳው ይህ የርህራሄና የህዝብ ፍቅር እሳቤ በዶ/ር ልሳነወርቅ ብቻ ሳይወሰን ዛሬ ላይ ዘርፈ ብዙ ሙያተኞችን አካትቶ፣ አድማሱን አስፍቶ እና ህብረተሰቡን በባለቤትነት አሳትፎ የብዙዎችን እንባ እያበሰ ይገኛል። ድርጅቱ አገልግሎቱን ከደቡብ ኢትዮጵያ አልፎ አሁን ላይ ወደ አዲስ አበባ እና ጋምቤላ ክልል በማስፋፋት ላይ ይገኛል።
​
​ሪዲዮ ኢትዮጵያ በዋናነት የሚያከናውናቸው ሰብአዊ ስራዎች ሁለንተናዊ የህይወት ለውጥ የሚያመጡ ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል።

👉 ​ሁለንተናዊ ጤና እና የጤና እኩልነት
👉 ​የአደጋ እና አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ
👉 ​ንጹህ ውሃ፣ ንጽህና እና አካባቢ ጥበቃ
👉 ​የስነ-ምግብ እና የምግብ ዋስትና
👉 ​የስነ-ልቦና እና የአእምሮ ጤና ድጋፍ
👉 ​የዲጂታል ጤና መፍትሄዎች
👉 ​የህጻናት ጥበቃ፣ ከለላ፣ የሴቶች እና የወጣቶች ማበቃት
👉 ​ትምህርት እና የማህበረሰብ አቅም ግንባታ ስራዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው።

​ዶ/ር ልሳነወርቅ እና ሪዲዮ ኢትዮጵያ ያከናወኗቸውግዙፍ የበጎ አድራጎት ስራዎች ከሀገር አልፈው በጋቪ (Gavi’s VaccinesWork)፣ በHealthy Lungs for Life 2026 እና በሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች እውቅና እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

​ዛሬ በዓለም አቀፍ መድረክ ለተሰየሙት የሰብአዊነት አርአያ ዶ/ር ልሳነወርቅ ሆንሴቦ ድምፃችንን በመስጠት ለሰብዓዊነት የሚቆሙትን ለማነሳሳት ጭምር እናበረታታ፤ ድምፅ ለመስጠት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ👇

humanitarian-hero-award

​Voice of Marginalized Community – WT Media