GridArt_20261017_142209245

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ሕዝብ ምክር ቤት ዶክተር መሠረት በቀለን አዲስ ከንቲባ አድርጎ ሾመ፤ የአመራር ሽግሽጉ በክልሉ በስፋት መቀጠሉ ተገለፀ

​የዎላይታ ሶዶ ከተማ ሕዝብ ምክር ቤት ባካሄደው 2ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ፣ ዶክተር መሠረት በቀለን የከተማዋ አዲስ ከንቲባ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።

​በከተማ አስተዳደሩ ይህ የአመራር ለውጥ የተደረገው፣ በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ በተደጋጋሚ ሲነሱ የነበሩ የመልማት ጥያቄዎችን እና የተስተጓጎሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል።

​ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው፣ ይህ የአመራር ሽግሽግና መልሶ የማደራጀት እንቅስቃሴ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

​በተጨማሪም የከተማው ሕዝብ ምክር ቤት በዚሁ ጉባኤው፣ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሚመደቡ የሥራ ኃላፊዎችን ሹመት መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል።

​WT Media በአዲሱ አመራር የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን እንዲሁም የሕዝብ ጥያቄዎች የሚሰጣቸውን ምላሾች ክትትል በማድረግ መረጃዎችን ማቅረቡን ይቀጥላል።