GridArt_20261017_152741191

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ ህዝብ ምክር ቤቶች ባካሄዷቸው አስቸኳይ ጉባኤዎች አዳዲስ የዞን ዋና አስተዳዳሪዎችንና የከተማ ከንቲባዎችን መሾማቸውን አስታውቋል።

​በዚሁ መሠረት በክልሉ በተካሄደው ሰፊ የአመራር መልሶ ማደራጀትና ሽግሽግ የተቀመጡ አዳዲስ አመራሮች፦

​በጋሞ ዞን እና አርባምንጭ ከተማ፦

​አቶ ገዛኸኝ ጋሞ — የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
​ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ መለሰ — የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

​በጌዴኦ ዞን እና ዲላ ከተማ፦
​ዶክተር መስፊን ደምሴ — የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
​አቶ ብዙአየሁ ታደሰ — የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

በዎላይታ ሶዶ ከተማ

​የዎላይታ ሶዶ ከተማ ሕዝብ ምክር ቤት ባካሄደው 2ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ፣ ዶክተር መሠረት በቀለን የከተማዋ አዲስ ከንቲባ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።

​በጎፋ ዞን፦
​አቶ በላይነህ ባህሩ — የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት ባካሄደው 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው በሙሉ ድምፅ ተመርጠዋል።

​በኣሪ ዞን፦
​አቶ አፌዶ ወርቁ — የኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት በጂንካ ከተማ ባካሄደው 4ተኛ ዙር 14ተኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾመዋል።

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደረጃ የተጀመረው ይህ የአመራር ሽግሽግ በየአካባቢው ህዝብ ዘንድ በተደጋጋሚ ሲነሱ የነበሩ የመልማት ጥያቄዎችን እና የተስተጓጎሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል።

​WT Media በአዲሱ አመራር የሚከናወኑ የልማትና የህግ የበላይነት ማስከበር ሥራዎችን እንዲሁም የህዝብ ጥያቄዎች የሚሰጣቸውን ምላሾች ክትትል በማድረግ መረጃዎችን ማቅረቡን ይቀጥላል።

Voice of Marginalized Community – WT Media