በዎላይታ ሶዶ ከተማ የግብር አሰባሰብ አፈፃፀም ዙሪያ የተፈፀመው ድብደባና ሰብዓዊ መብት ጥሰት ውዝግብ ማስነሳቱ ተገለፀ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሰሞኑ የገቢዎች መምሪያ እና የጸጥታ አካላት የተካሄደው የግብር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ቁጥጥር ሂደት “ፖሊስ ድብደባ ፈጽሟል እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል” የተባለው ከፍተኛ አነጋጋሪ ጉዳይ ስለመሆኑ ተመልክተናል። 

በጉዳዩ በ«ሊድያ ባህላዊ ምግብ ቤት» ዙሪያ የተፈጠረውን ክስተት የሚያሳይ የደህንነት ካሜራ (CCTV) ቪዲዮ፣ የከተማው ፖሊስ መምሪያ ያወጣውን ይፋዊ መግለጫ እና ከህብረተሰቡ የተነሱ ስጋቶችን ያካተተ ዜና WT Media ከዚህ በታች ያቀርባል።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ፖሊስ ድብደባ ፈጽሟል እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል በሚል የተሰራጩ መረጃዎች ከእውነታው የራቁ እና የክስተቱን ሙሉ ሁኔታ የማያንጸባርቁ ናቸው።

ቁጥጥሩ የተካሄደው የልድያ ባህል ምግብ ቤት የቫት ደረሰኝ ባለመቁረጡና ለደንበኞች ባለማቅረቡ ምክንያት በገቢዎች መምሪያ የቁጥጥር ግብረ ኃይል ጥያቄ መሆኑ ተገልጿል።

የፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/18 እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 22/2016ን በመጥቀስ፣ የሽያጭ ደረሰኝ አለመስጠት እና የታክስ ስርዓትን ማዳንቀፍ እስከ እስራት እና ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት የሚያስከትል ወንጀል መሆኑንም በመግለጫው ጠቅሷል። 

የጸጥታ አካላት ግለሰቧን በሕጋዊ ሥርዓት ለማነጋገር ቢሞክሩም ፍቃደኛ ባለመሆኗ እና የሕግ አስከባሪዎችን ሥራ ለማደናቀፍ የሚያስችል ባህሪ በማሳየቷ እርምጃው መወሰኑን የከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ገልጸዋል። ፖሊስ ህብረተሰቡ የተዛቡ መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲመለከት ጥሪ አቅርቧል። 

በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩት “ድብደባ ተፈጽሟል፣ ሰብአዊ መብት ተጥሷል” የሚሉ መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን በመግለጽ ህብረተሰቡ የተዛቡ መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲመለከት አሳስቧል።

በሌላ በኩል የደህንነት ካሜራ (CCTV) ቪዲዮ እና ከህብረተሰቡ የሚነሱ አስተያየቶች የሂደቱን አፈጻጸም ይቃወማሉ።

WT Media የተመለከተው ቪዲዮው ላይ ግለሰቧን በኃይል ከመሬት እየጎተቱ ወደ ፓትሮል (የፖሊስ ተሽከርካሪ) ለማስገባት የተደረገው ጥረት ሂደት ከቀልብ ጋር የሚሰራ የቁጥጥር ሂደት ሳይሆን ከፍተኛ ውጥረት የነገሰበት መሆኑ ተመልክቷል።

WT Media የተመለከተው ቪዲዮው ላይ ግለሰቧን በኃይል ከመሬት እየጎተቱ ወደ ፓትሮል (የፖሊስ ተሽከርካሪ) ለማስገባት የተደረገው ጥረት ሂደት

ህግን ማስከበር አስፈላጊ ቢሆንም፣ ሂደቱ የዜጎችን ሰብአዊ ክብር (በተለይም ሴቶች በህግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ ሊጠበቅ የሚገባውን ስነ-ምግባር) ያላካተተ መሆኑ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ስሜታዊነትና ቅሬታን ፈጥሯል።

የቪዲዮ ምስል እንደሚያሳየው በቦታው ላይ በርካታ የጸጥታ አካላት እና የግብረ-ኃይል አባላት ተሰብስበው ይገኛሉ። ሁኔታው ከቀልብ ከሚሰጥ የቁጥጥር ሂደት ይልቅ ከፍተኛ ጫና እና ውጥረት የነገሰበት ይመስላል። በቪዲዮው ላይ ግለሰቧን (የባህላዊ ምግብ ቤቱን ባለቤት/አስተዳዳሪ) በኃይል ከመሬት እየጎተቱ ወደ ፓትሮል (የፖሊስ ተሽከርካሪ) ለመጫን የሚደረገው ጥረት በግልጽ ይታያል።

ህግን ማስከበር የየትኛውም መንግሥታዊ አካል ግዴታ ቢሆንም፣ ሂደቱ ሴት አክባሪና ሰብአዊ ክብሯን የጠበቀ እንዳልነበረ ቪዲዮው ያሳያል። በcrowd (በበርካታ ሰዎች) ተከቦ የሚፈጸም ውትወታ እና ጎተታ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ስሜታዊነትን መፍጠሩ ተፈጥሯዊ ነው።

ይህንን ጉዳይ ከሀገራዊ እውነታ እና ከህዝብ ጥቅም አንጻር ስንመረምረው ሁለት ሐቅዎችን ጎን ለጎን ማየት ይገባል።

ሀገርን መገንባት፣ መሰረተ ልማቶችን ማሟላት እና ህዝባዊ አገልግሎቶችን መስጠት የሚቻለው ከንግዱ ማህበረሰብ ከሚሰበሰብ ግብርና ታክስ ነው። ስለዚህ በሶዶ ከተማ የተጀመረው ግብርን በህጋዊ መንገድ የማስከበር ንቅናቄ ትክክለኛ፣ ተገቢ እና ሊቀጥል የሚገባው የልማት ምሰሶ ነው። ህግ ማክበር የሁሉም ዜጋ ግዴታ ነው።

የንግዱ ማህበረሰብ ህግ አክብሮ ግብሩን መክፈል አለበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ የጸጥታ አካላት ህግን ሲያስከብሩ የዜጎችን ሰብአዊ ክብርና ነጻነት ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል። ህግ ማስከበርና ሰብአዊ ክብር ማክበር ተቃራኒዎች ሳይሆኑ አብረው መሄድ የሚገባቸው የዲሞክራሲ ማዕዘኖች እንደሆኑ በርካቶች እየገለፁ ናቸው።