GridArt_20261105_224915118

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ዞን ዴሣ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በአንዲት ዜጋ ላይ የአስገድዶ መድፈርና የጠለፋ ወንጀል የፈጸሙ ሁለት ግለሰቦች በጽኑ እስራት እንዲቀጡ የዴሣ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል።

​ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. በዋለው የወንጀል ችሎት ውሳኔ ያገኘው ይህ መዝገብ፤ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2026 (ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም.) የተፈጸመውን ወንጀል መሠረት ያደረገ ነው።
​
​እንደ ፍርድ ቤት መዝገብ እና የፖሊስ ምርመራ የግል ተበዳይ ወጣት አሜሪካን አየለ ከቤተክርስቲያን ፕሮግራም በመመለስ ላይ እያለች በዴሣ ከተማ ቶራ ኦፎሬ ቀበሌ «አምቢያ ጉታራ» በተባለ ልዩ ቦታ ላይ 1ኛ ተከሳሽ አለማየሁ ኡኩሞ እና 2ኛ ተከሳሽ ግርማ ጃግሶ መንገድ ላይ ጠብቀው አፏን በኃይል በማፈን አፍነው አቆይተዋታል።

​በመቀጠልም ተከሳሾቹ ተበዳይን በሞተር ባጃጅ ወደ ዱጉና ፋንጎ ወረዳ ብጠና ከተማ ከወሰዷት በኋላ፣ በሕዝብ ትራንስፖርት እስከ ሐዋሳ፣ ከሐዋሳ ወደ ሻሸመኔ፤ በመጨረሻም ወደ ሐላባ ከተማ ወስደዋታል።

1ኛ ተከሳሽ አለማየሁ ኡኩሞ አስቀድሞ ተከራይቶ ወደነበረው አንድ ክፍል ቤት ካስገባት በኋላ፤ በሌሊት 6:00 ሰዓት ላይ ልብሷን በማውለቅ በኃይል አስገድዶ እንደደፈራትና ጠለፋውን እንደፈጸመ በሰው እና በሕክምና ማስረጃ ተረጋግጧል።

​2ኛ ተከሳሽ ግርማ ጃግሶ ደግሞ ተበዳይ እንዳትጮህ አፏን አፍኖ በመያዝ እስከ ብጠና ከተማ ድረስ በመውሰድ በጠለፋ ወንጀሉ መሳተፉ ተረጋግጧል።

​የዴሣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ታክቲክ ወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ መክትል ሐለቃ ሉቃስ ወርቁ እንደገለጹት፤ 1ኛ ተከሳሽ ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ በሐላባ ከተማ ተደብቆ እያለ በፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል።

ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በሰው እና በሕክምና ማስረጃ በማደራጀት ለዴሣ ከተማ አስተዳደር ዓቃቤ ሕግ ልኳል።

​ዓቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምሮ ለዴሣ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. (2019) በዋለው የወንጀል ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የሚከተለውን የጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።

​1ኛ ተከሳሽ አለማየሁ ኡኩሞ፦ በአስገድዶ መድፈርና ጠለፋ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ13 (አሥራ ሦስት) ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ፤

​2ኛ ተከሳሽ ግርማ ጃግሶ፦ በጠለፋ ወንጀል ተሳታፊ በመሆኑ በ6 (ስድስት) ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖባቸዋል።

​WT Media | Voice of Marginalized Community