በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በተካሄደው የጤና ዘርፍ የምክክር መድረክ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ ተገኝተው እንደተናገሩት፣ በየትኛውም ወረዳ የተሽከርካሪ እጥረት ቢኖር እንኳ ለአናቶች የጤና እንክብካቤ እና ለህይወት አድን ስራዎች የተመደበ አምቡላንስ በምንም መልኩ ለሌላ ስራ መዋል እንደማይችል ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም በወረዳዎች ደረጃ የተሽከርካሪ እና የሞተር እጥረት መኖሩ ቢታወቅም፣ በጋራ መታለፍ (ኮምፕሮማይዝ) የማይደረጉ «ቀይ መስመሮች» መቀመጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በዚህም መሰረት ለአናቶች የጤና እንክብካቤ እና እናቶች አደጋ ውስጥ እንዳይገቡ የተመደበ አምቡላንስ በምንም መልኩ ለሌላ ስራ መዋል እንደማይችል በጥብቅ ተነግሯል።
ይህንን ትዕዛዝ የሚጥስ ማንኛውም አካል ላይ ተጨማሪ ግምገማ እንደማያስፈልግ ተገልጾ፤ ወዲያውኑ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እና ለዞን አስተዳደር እንዲሁም ለፓርቲው ሪፖርት እንዲደረግ ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፏል።
እናትና ህጻናትን ከሞት አደጋ ለመታደግ የተመደበን አምቡላንስ ለግል ወይም ለሌላ ውጪ ስራ ማዋል ሰብአዊነትን እና ህግን ከባድ ጥሰት ውስጥ የሚከት አደገኛ ተግባር ነው። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳረጋገጡት፣ ከህይወት አድን ስራዎች ጋር በምንም መልኩ መደራደር የማይቻል በመሆኑ፤ ይህንን ጥብቅ «ቀይ መስመር» የሚጥሱ አካላት ላይ ያለ ምንም ማመንታት ወዲያውኑ ሕጋዊና ተቋማዊ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል።
WT Media | Voice of Marginalized Community