በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሰራር እና አስተዳደር ዙሪያ ከፍተኛ ውዝግብ እና የቅሬታ ድምጾች እየተሰሙ ይገኛሉ።
ተቋሙ ከቀድሞው አሰራሩ ያልተላቀቀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ የበጀት አጠቃቀም፣ የቁሳቁስ ድጋፍ እጥረት እና የዳኞች የስራ ሁኔታ ከባድ ችግር ውስጥ መውደቁን በ WT Media ከውስጥ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የተቋሙ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች እንደሚያብራሩት በሌሎች ሴክተሮች የተደረጉ ለውጦች አበረታች ቢሆኑም፤ በፍትህ አካሉ በተለይም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ደረጃ ያለው አሰራር አሁንም ፍትህን እና የሰራተኛውን መብት የሚያጓድል መሆኑ ከፍተኛ ቅሬታ አስነስቷል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሐምሌ ወር ጀምሮ እስከ 8.5 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የሥራ ማስኬጃ budget ለክልሉ ቢሮዎች ቢላክም፣ ለምደብ ችሎቶች (ለአርባምንጭ እና ዎላይታ) ምንም ዓይነት ገንዘብ ሳይደርስ ቀርቷል።
ከጎፋ፣ ከዎላይታ ሶዶ እና ከአርባምንጭ ከተማ ውጭ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሰሩ ጉዳዮች (በተለይ ማረሚያ ቤት ያሉ እስረኞች ጉዳይ) በብቃት እየተሰሙ አይደለም። ተዘዋዋሪ ችሎቶች በመቋረጣቸው እና ፋይሎች በመከማቸታቸው ፍርድ ቤቱ ከፍትህ አሰጣጥ ይልቅ ለዜጎች ተጨማሪ እንግልት እየሆነ መጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ውስጥ ውሃ እንኳን መግዛት እስከማቻቻል የሚደርስ የбጀት እጥረት አለ።
ለመጣራት የተከጠሩ መዛግብት እና ሰራተኞች አበል ባለመከፈሉ ተቸግረዋል፤ የውስጥ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችም በገንዘብ እጥረት ሳቢያ ከባድ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ።
በፍርድ ቤቱ ውስጥ ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ እጅግ ኋላቀር መሆኑ ተገልጿል።
በ2017 ዓ.ም. አዲስ የተሾሙ 20 ዳኞች ጨምሮ አብዛኛዎቹ ዳኞች እስካሁን ኮምፒውተር አልተገዛላቸውም። በዚህም የተነሳ ስራዎቻቸውን በሰነድ እና በእጅ እየጻፉ ይገኛሉ።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ዳኞች ላፕቶፕ እና ዋይፋይ የሌላቸው ሲሆን፤ የሻይ፣ ቡና እና የውሃ бጀት አጠቃቀም ሂደትም ግልጽነት የጎደለው እና ለዳኞች ተገቢውን ድጋፍ የማይሰጥ መሆኑ ተነስቷል።
የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ዳኞችን ሰብስበው ችግሮቻቸውን ለመሰማት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተገልጿል። አመራሮቹ ከዳኞች ጋር የሚገናኙት በወር አንድ ጊዜ በሚደረግ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ብቻ በመሆኑ፣ ዳኞች የውስጥ ችግሮቻቸውን አውርዘው መፍትሄ ማግኘት አልቻሉም።
ከዚህ የተነሳ እድሜያቸው 55 ዓመት የሞላ ዳኞች የስራ መልቀቂያ አስገብተው በምርጫቸው መሰረት የሚገባቸውን የቲክ ገንዘብ ይዘው ለመውጣት (ለመሰናበት) እየተዘጋጁ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ልምድ፣ እውቀት እና ንጽህና ያላቸውን ባለሙያዎች ከፍርድ ቤቱ በማስወጣት ላይ ይገኛል።
ፍትህ እንዲሰፍን የሚጠይቁ እና ችግሮችን በግልጽ የሚያነሱ ወጣት ዳኞች ላይ አስተዳደራዊ ጫናዎች እና ማስፈራሪያዎች እየተደረጉባቸው መሆኑ ተመላክቷል።
በክልሉ በሚገኙ ሌሎች ተቋማት እና ሴክተሮች ላይ የተወሰኑ የመልካም አስተዳደር እና የለውጥ እርምጃዎች ውጤት እያሳዩ ቢሆንም፣ የፍትህ አካሉ በተለይም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሁንም ከፍተኛ ጩኸት የሚሰማበት እና አፋጣኝ ሬፎርም (እድሳት) የሚያስፈልገው ተቋም ሆኗል።
ሕግ አስተርጓሚው አካል ራሱ በውስጣዊ ቀውስ እና በሀብት እጥረት ውስጥ እያለ ፍትህ ማስፈን ስለማይችል፣ የሚመለከታቸው የክልሉ አካላት ጉዳዩን አጣርተው አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡበት የውስጥ አካላት ለ WT Media በሰጡት መረጃ አበክረው ይጠይቃሉ።
WT Media | Voice of Marginalized Community