1794251942426


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደመወዝ አከፋፈል ስርዓት ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ የሚገኘውን ሕገ-ወጥ ቅጥር እና የአስተዳደር ክፍተት ለመቅረፍ ጥብቅ ማጣራቶች እየተደረጉ መሆኑ ተሰምቷል።

ጉዳዩ የተነሳው በዎላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደው የክልል አቀፍ የፋይናንስ ሴክተር የንቅናቄ መድረክ ላይ ነው።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ነቢዩ ቤዛ እንደገለጹት፤ በክልሉ የደመወዝ አከፋፈል ሂደት ላይ ከባድ ጫና የፈጠረውን ሕገ-ወጥ ቅጥር ለማጣራት እና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሰፊ ስራ ተጀምሯል።

​ምክትል ኮሚሽነሩ አያይዘውም፣ በአሁን ሰዓት የመደብ መታወቂያ ቁጥር የማሰባሰብ ስራ ወደ 80 በመቶ ገደማ መድረሱን ጠቁመዋል።

​በክልሉ መረጃ ቋት ውስጥ ከ180 ሺህ በላይ ሰራተኞች እንዳሉ ቢታወቅም፤ በተለያየ መንገድ በፔሮል (የደመወዝ መክፈያ ዝርዝር) ይከፈላቸው ተብሎ ወደ ተቋሙ የሚደርሰው መረጃ ግን ከ200 ሺህ በላይ ሰራተኞች እንዳሉ ያሳያል።

​ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ምንም አይነት ትክክለኛ የመደብ መታወቂያ ቁጥር ሳይኖራቸው ያለስራ ደመወዝ እየተከፈላቸው እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

​አቶ ነቢዩ ቤዛ አክለውም፣ እነዚህን ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች በዝርዝር ካጣሩ በኋላ የሚወሰዱትን እርምጃዎች አስመልክቶ፦

​1. ተገቢውን የትምህርት ዝግጅት እና መመዘኛ የሚያሟሉትን በቀጥታ ወደ ስራ የማሰማራት ስራ እንደሚሰራ፣

​2. መስፈርቱን የማያሟሉ ሆነው ከተገኙ ግን በመንግስት ሰራተኞች የሽኝት መመሪያ መሠረት ወደ ሌሎች አማራጭ የስራ መስኮች የማሻገር ስራ እንደሚከናወን ገልጸዋል።

እንደ ዎላይታ ቴሌቪዥን ዘገባ ​ይህ ችግር በአሁኑ ወቅት በክልሉ በመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ አከፋፈል ስርዓት ላይ ለሚታየው የбጀት እጥረት እና መዋቅራዊ ጫና ዋናው ምክንያት መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል።

​WT Media | Voice of Marginalized Community