በሰሜን ኢትዬጲያ የህውሃት አሸባሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት ከ 1.4 ሚሊዬን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ ገለፁ።
በግጭቱም ከ 7ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን እና ከ 4ሺህ በላይ መምህራን ከስራ ገበታ ውጪ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም አሸባሪው ቡድኑ ግጨቱን ወደ አጎራባች አማራ እና አፋር ክልሎች በማስፋት ከ ሰባት መቶ በላይ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረጉም ተገልጿል።
ቡድኑ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ከማድረስ ባሻገር ህፃናትን ወደ ጦርነት እየማገደ በመሆኑ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እውነታውን ተገንዝቦ ድርጊቱን እንዲያወግዝ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።
በቀጣይም ትምህርት ሚኒስቴር የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ በመገንባት እና ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት በመመለስ ሂደት ውስጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡Wolaita Timese/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 26/12/13 E.C , Sodo, #Ethiopia🇪🇹
