ኮሌጁ ቅዳሜ ማለትም 29/2013 ዓ.ም በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር በዲፕሎማ፣ በድግሪና ማስተርስ ፕሮግራም በዘጠኝ ካምፓሶች ያሰለጠናቸውን 2864 ተማሪዎችን እንደምያስመርቅ ከኮሌጁ ርጅስትራልና አልሙኒ ዳይረክቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዕለቱ የምርቃ ሰነስርዓት በኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (EBC) ቴለቪዥን በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዳሞታ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ መቀመጫውን ዎላይታ ሶዶ አድርጎ በዞኑና በተለያዩ ክልሎች ከአስራ ሶስት ካምፓሶች በላይ ላይ እውቅና ባገኘባቸው በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት ዘርፍ በዲፕሎማ፣ በድግሪና ማስተርስ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ የሚገኝ መሆኑን ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
