የኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን በዎላይታ ሶዶ ከተማ አቅመ ደካማ ለሆኑ 1ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ኢትዮ ቴሌኮም በሀገሪቱ ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴ ከመዘርጋትም በተጨማሪ በተለያዩ ዘርፎች ህብረተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ከመንግስት ጋር ተቀናጅተው እየሠራ መቆየቱን የሪጅኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሹመ አብሽሮ ተናግረዋል።

አቶ ሹመ የዛሬ ድጋፍ ሪጅኑ በተለያዩ አከባቢዎች አቅመ ደካማ ለሆኑ ተማሪዎች ቁሳቁስ ድጋፍ መርሃ ግብር አካል መሆኑን ተናግረው ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችም በትምህርታቸው በርትተው ትልቅ ተስፋ ሰንቀው ሊማሩ ይገባል ብለዋል።

አቶ መርክኔ ማለዳ የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሀገሪቱ የትምህርት ጥራትንና ፍትሐዊነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በዘረጋችበት መስመር የዎላይታ ሶዶ ከተማ አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ሥራ መሠረተ ባደረገ መልክ ለጥራት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህ ወቅት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ለማድረግ ለተጀመረው ርብርብ የኢትዮ ቴሌ ድጋፍ አቅም ይሆናል ብለዉ በማመስገን ተማሪዎችም በትምህርታቸው ተጠናክረው የዛሬ ጭንቅና ችግር ታርክ እንደሚሆን አውቀው ሊማሩ ይገባል ብለዋል።

የትምህርት ቁሳቁስ ያገኙ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች በድጋፉ መደሰታቸውን ገልፀው መንግስት ልጆቻችን ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ሊደግፈን ይገባልም ብለዋል።