የኮንሶ ጉዳይ “የኔ ጉዳይ ነው!” በማለት የህዝቡ ልማት፣ ሠላምና መልካም አስተዳደር ስርዓት ላይ አንድ መሆን አለብን ሲሉ የኮንሶ ምሁራን ተናገሩ።
“2014 ዓ.ም የኮንሶ ህዝብ የካሳ ዘመን ይሁንልን” በሚል የተካሄደው የምሁራንኮንፍራንስበሠላም ተጠናቀቀ።
በምሁራንና አመራሩ መካከል እርስ በእርስ መጠራጠሮች እንደ ችግር የሚታዩ ሲሆን፤ በተለያዩ አከባቢዎች ያሉንን አመራሮች መደገፍ አለብን በማለት ቤቱ መክሯል ሲሉ የማጠቃለያ ሃሳብ ያቀረቡት አቶ ኩማቸው ኩሴ ተናግረዋል።
አመራሩ ህዝብ ውስጥ ያለውን ሀሳብ ማዳመጥ አለበት፣ አመራሩ በስነ ምግባሩ አርዓያ መሆን አለበት፣ የፍትህ አካላት ገለልተኛ እንዲሆኑ ምሁራኑ ጠይቀዋል።
ሠላምን በመገንባትና አብሮነትን በማጠናከር ከአጎራባች ልዩ ወረዳዎችና መዋቅሮች ጋር ሠላማዊ ግንኙነት እንዲጠናከርና በሰገን ዙሪያ ወረዳ የተከሰተውን ችግር በተለየ ትኩረት የህዝሁ ሠላም እንዲጠበቅ እንሰራለን ብለዋል።
ይህ ታላቅ የምሁራን ኮንፍራንስ እንዲንቀራረብ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ተናግረው፤ የአብሮነት የውይይት መድረኩ መዘገየቱ ህብረተሰባችንን እንደጎዳ ምሁራኑ አስታውቀዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበዬሁ በውይይት ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ሲቪል ሰርቫንቱ በተሰማራበት የሙያ ዘርፍ ሁሉ ህዝቡን ለማገልገል በቁርጠኝነት እዲሰሩም አሳስበዋል።
እንደ ኮንሶ ዞን አንደኛው የምሁር ኮንፍረንስ መሆኑን የሚያበስር የአንድ ቁጥር ሻማ በዞን የሠላምና እርቅ ኮሚቴ አባቶች አጃብነት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበዬሁ ተለኩሷል።
በኮንሶ ዞን የመዋቅር ጥያቄ ውስጥ ሚና የነበራቸው አቶ ገመቹ ገንፌ በበኩላቸው እስካሁን ከአመራሩ ጋር የመጣንበት አለመግባባቶች ቀርተው በፍቅር ተጋምደን የኮንሶን ሠላምና ልማት ልናረጋግጥ ይገባል ብለዋል።
የኮንሶ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም ከምሁሩ ጋር ለነበረው አለመቀራረብ ይቅርታ ጠይቀዋል።
እንደ ዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዘገባ “የኮንሶ ምሁራን አንድነት ለኮንሶ ልማት የስብሰባ አዳራሽ” እና የኮንሶ የጎበዝ ተማሪዎች ትምህርት ቤት” ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በአስተዳዳሪው አቶ ዳዊት ገበዬሁ እና በልማት ማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽብሩ ሲካ በጋራ አስቀምጠዋል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡Wolaita Timese/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 01/13/13 E.C , Sodo, #Ethiopia🇪🇹

