በሙዚየሙ ውስጥ የዎላይታ ብሔርን ትውፊት የሚገልጹ ባህላዊና ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ከ350 የሚበልጡ ቅርሶች እንደሚገኙ ተገልጿል።
“ቅርስ ያለው ታሪክ አለው” በሚል መርህ በ2012 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ-ገንደባ ካምፓስ የተመሰረተው ይህ ሙዚየም በዘርፉ ጥናትና ምርምር ከማካሄድ ባሻገር ቅርሱን ለጎብኝዎች በማስተዋወቅ የብሔሩ ቱባ ባሕል ለማስተዋወቅ ብሎም ለቀጣዩ ትውልድ ባሕልና ታሪክን ለማስተላለፍ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
በጉብኝቱ እና ችግኝ ተከላው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጀነራሎች፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል ሲል የዩንቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ዳይሮክተሬት ዘግቧል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡Wolaita Timese/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 02/13/13 E.C , Sodo, #Ethiopia🇪🇹


