ባለፈው ወር ከአረካ ከተማ ሌላኛ ወደ ፊጦ መሻገሪያ ድልድይ መደርመስን ተከትሎ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እስከ ቦታው ድረስ ሄዶ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል።
አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ሌላኛው የጣዲሳ መሻገሪያ ድልድይ በመባል የሚታወቅ በአረካ ከተማ መደርመሱን ነዋሪዎች ከስፍራው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።
ይሄ በከፍተኛ የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ የተገነባው ድልድይ አለአግባብ እንዲባክን ያደረጉ አካላት በህግ ተለይቶ እንዲጠይቅም ከስፍራው መረጃውን ያደረሱ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
አንድ ድልድዩ ወይም መሰል ግንባታ ከተገነባ 10 ዓመት ባልሞላ ጊዜ በጥራት ጉድለት ከተበላሸ በcivil code አንቀፅ 3282 (1) እና በደቡብ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን አፈፃፀም ደንብ ቁጥር 153/ 2009 አንቀፅ 74 መሰረት ሥራ ተቋራጭም ሆነ ጥራት ተቆጣጣሪ አካል ተለይተው በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ ይላል።
ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በከተማዋ በመጀመሪያ ዙር የወደቀው የፊጦ መሻገሪያ ድልድይ ጉዳይ በምን ምክንያት ነው የተደረመሰው የምለውን የመጨረሻ የባሉሙያ ትንተና እየተጠባበቀ ሲሆን አሁንም በከተማዋ ለሁለተኛ ጊዜ የተደረመሰው ሌላኛው የጣዲሳ መሻገሪያ ድልድይ ጉዳይ ዝርዝር መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት አጣርቶ የሚያቀርብ ይሆናል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 03/13/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹

