ቡንጌ ቡሩንጄ በልጅነቱ በትምህርት እጂግ ጎቤዝና ወደ ዩንቨርስቲ ማስገቢያ ውጤት ከፍተኛ አራት ነጥብ በማምጣት እውቁን አዲስአበባ ዩንቨርስቲ 1993 ዓ.ም በመቀላቀል የኢኮኖሚክስ ትምህርት በመከታተል በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቀ እጂግ በትምህርት ባለምጥቅ ጭንቅላት ባለቤት መሆኑን ከህይወት ታሪኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ቡንጌ ቡርንጄ ከትምህርት ጉብዝና በተጨማሪ ለጥበብ ስራዎች እጂግ ቅርብ የሆነ ሰው በመሆኑ በዩኒቨርስቲ ተማሪ ሆኖ የጀመረውን ስራ በ1998 ዓ.ም መጀመሪያ አከባቢ ለዎላይታ እና አከባቢው አስደማሚ የሆነ “ካዎ ጦና” የተሰኘ የጥበብ ስራ ይዞ ብቅ አለ።
2ኛ አልቤሙን “ሃሎ ሳወዝ ኢትዮጵያ” በሚል የኦሞቲክ ቤተሰብ አርቲስቶችን አስተባብሮ ለመስራት የቻለ ያልተነገረለት የጥበብ ባለቤት መሆኑ ይነገርለታል።
አርቲስት ቡንጌ ቡርንጄ ለብሄሩ ብቻ ሰይሆን በደቡብ ኦሞ ዳሰነች ወረዳ ከሶስት መቶ በላይ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ስሞቱ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ “ታናሞ” የሚል ነጠላ ዜማ ከብዙ ስራዎች ጥቂት ነው።
ሌላው “ጃላ ጋራንጌ” በሚል በዎላይታ ህዝብ ዘንድ ጥልቅ ክብርና አድናቆት ለነበረው አቶ ፍሬው አልታዬ ማስታውሻ የሰራው ስራ እጂግ ከሚወደዱ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
አርቲስት ቡንጌ ቡሩንጄ የወያኔ የበላይነት በነገሰበት ወቅት ስርዓቱን በአደባባይ በመተቸት በሰራው ስራ ብዙ ፓለቲካዊ ጫና እንደደረሰበት ከራሱ አንደቤት ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልፀዋል።
በዎላይታ እና አከባቢው በወቅቱ ለሰራ ወደ ሌላ ቦታ ስንቀሳቀሱ ሰብዓዊ ክብራቸው በሚነካ ሁኔታ በመሆኑ “ካሎ ካሚያራ” ብሎ በሰራው ስራ ድርጊት እንዲቆም ያደረገ አርቲስት ነው።
ቡንጌ ቡርንጄ አርቲስት፣ ገጣሚ፣ ድምፃዊ፣ ኢኮኖሚስት እና ባለብዙ ጥበብ ተስጦዖ ባለቤት ነው። አዲስ ሰራ ይዞ ለመምጣት እየሰራ ይገኛል።
ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ለሀገር በሙያቸው በጎ ስራ ላበረከቱ አርቲስቶች ጥሪ በተደረገበት አርቲስት ቡንጌ ቡሩንጄም ጥሪ መድረሱን አጫውተውናል።
ሙሉ ቃለ መጠየቅ በቅርቡ በዌብሳይታችን ይጠብቁ🙏
