ዲስትሪክቱ ያለፉት ሁለት ወራት አፈጻጸም በመገምገም የ2014 ዓ/ም የግብ ስምምነት ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሥራ አስኪያጆች ጋር ተፈራርሟል።
በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የሶዶ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ያይና ድስትሪክቱ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ከተለያዩ ምንጮች ከ149 ሚሊዮን ብር በላይ ቁጠባ ማሰባሰቡንና ከ24 ሞሊዮን ብር በላይ ብድር ስርጭት ማካሄዱን ገለጽዋል፡፡
ዲስትሪክቱ ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ማስመለሱንና አስቸጋሪና ውዝፍ ውስጥ ከተባሉ የብድር ዓይነቶች ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ማስመለሱን አቶ ተመስገን አክለው ገለጸዋል፡፡
በድስትሪክቱ አንዳንድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ህዝባዊ መሰረት ያለውን በተለይ በተቋሙ መረጋጋት የሚችል ቁጠባ ከማስቆጠብ አንጻር የሚታየውን ክፍተት ለመሙላትና የብድር አመላለሱን ወጥ በሆነ አሰራር 95 ከመቶ አድርጎ ለመምራት በላይ ቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
ብድር ወስደው ሳይከፍሉ ካስወዘፉ ደንበኞች በድርድር ለማስመለስና በእንብተኝነት ከቀጠሉ ግን ከአቃቤ ህግ ተቋም ጋር በመሆን በውሉ መሠረት የማስመለሱ ሥራ በህግ እንደሚሰራ ሥራ አስኪያጁ ተናግረውል፡፡
ህብረተሰቡ ሰርቶ ካሚያገኘው ገቢ በቋሚነት በመቆጠብና ቁጠባን ባህል በማድረግ ሊከሰት የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ችግር ራሱን እንዲከላከል አቶ ተመስገን አሳስበዋል፡፡
የተቋሙ ደንበኞች ብድር ከመውሰዳቸው በፊት ምን በመስራት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል የቢዝኔስ ዕቅድ በማውጣት እንዲበደሩና የተበደሩትን ገንዘብ በውሉ መሠረት መከፍል እንደሚገባቸው አክለው አሳስበዋል፡፡
እንደ ዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘገባ በ2014 ዓ/ም የዲስትሪክቱን ተግባር በዕቅድ ለመምራት የሚያስችልና በዕቅዱ መሠረት ካለተተገበረ ተጠያቂነትም የሚያስከትል የግብ ስምምነት የዲስትሪክቱ ሥራአስኪያጅ አቶ ተመስገን ያይና ከ27ቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጆች ጋር ተፈራርመዋል፡፡

