ከታች በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ተከታይ ያለው ግለሰብ መልዕክቱን ለማስተላለፍ ያያያዘው ፎቶ ትክክለኛ ነው?
በፌስቡክ እና ትውቴር ማህበራዊ መገናኛ ገፅ ላይ ከታች አንድ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ተከታይ ያለው ግለሰብ መልዕክቱን ለማስተላለፍ ያያያዘው ፎቶ ባለፈው 2013 ዓ.ም ታህሳስ ወር በዎላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ ድንገተኛ ቃጠሎ አንዲት እናት (ወይዘሮ የሺህ ቃልቦሬ) የጉዳቱን መጠን አይተው በማዘን ሲያለቅሱ የተነሱት ፎቶ መሆኑን አረጋግጠናል።
የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የተለጠፈው ፎቶ እና መልዕክቱ የማይገናኝ ስለመሆኑ ብቻ አረጋግጧል እንጂ የተላለፈውን መልዕክት አይደለም።
በወቅቱ ከታች እኚህ እናት በማዘን ለሌላው ርህራሄ ባሳዩበት በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ወደ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት መውደሙ ይታወሳል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡Wolaita Timese/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 02/01/14 E.C , Sodo, #Ethiopia🇪🇹
