ኢትዮጵያ የገጠማትን የህልውና አደጋ ተከትሎ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው በብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል መሰረታዊ የውትድርና ስልጠናን ያጠናቀቁ የሠራዊት አባላት ናቸው የተመረቁት።
ተመራቂ ወታደሮች በውጊያ ቴክኒክ ፤ በአካል ብቃት እንደዚሁም በሌሎችም መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር የታገዘ ወታደራዊ ስልጠና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ተመራቂ የሠራዊት አባላቱ የሚሰጣቸውን ማናቸውም ግዳጆች በብቃት በመወጣት ሀገርን ከውስጥ እና ከውጪ ወራሪ ለመጠበቅ ያላቸውን ዝግጁነት ተናግረዋል።
በምርቃት ስነ- ስርአቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መገኘታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።


