በዛሬው ዕለት ንቅናቄውን የዎላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ በይፋ አስጀምረዋል፡፡
የነጭ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት የሚደረገው ዘመቻ በብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት አማካይኝነት እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረ ዘመቻ ዋና ዓላማው በኢትዮጵያ በኩል ያለውን እውነት በአጭሩ ግልጽ በሆነ መንገድ ለአለም ማስረዳት ይሆናል።
በኢትዮጵያ ላይ በተሳሳተ መልኩ ሲሰራጭ የቆየው ሀሰት ፕሮፓጋንዳው ከእዉነት የራቀ መሆኑን ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳየት የሚያስችል ዘመቻ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
በዚህ ንቅናቀው ከዎላይታ ዞን ከሁሉም ወረዳ/ከተማ አስተዳዳር እስከ 25 ሺህ የሚደርሱ ወጣቶች ወደ ነጩ ቤተመንግስት የሚላከውን ደብዳቤ ፅፈው በዞኑ ደረጃ ሰብስበው ይልካል ተብሎ ይጠበቃል።
እንደ ዞኑ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ዘገባ ዘመቻው ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በመላው አገሪቱ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ጻፈውና ፈርሞ የሚያዘጋጁት ደብዳቤ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ይላካል፡፡
ከመላው ሀገሪቱ የተሰበሰበው ፓስታ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም እንደሚደርስ ተገልጿል።


