አደጋው የተከሰተው በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6፡30 በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ በር ሲሆን ከዲታ ወደ አርባምንጭ ስጓዝ የነበረ ህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ አይሱዙ መኪና ታርጋ ቁጥር 15216 ደህ ኮድ 3 የሆነ ኮድ 4 ኢት ታርጋ ቁጥር 30672 የሆነ ሀርድ ቶፕ መኪና ጋር በመጋጨቱ እንደሆነ ተገልጿል።
የአርባምንጭ ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት የከማውን ፖሊስ ጠቅሶ እንደዘገበው በትራፍክ አደጋው የ2 ሰዎች ህይወት ወዲያው ስያልፍ በ8 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት በ11 ሰዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት እና በወቅቱ በፔርማታ በነበሩ ባጃጆች ላይ ጉዳት ደርሷል።
የአደጋው መንስኤ በፍጥነት ማሽከርከርና ቅድሚያ ያለመስጠት እንደሆነ ተነግሯል።


