ለረጅም አመታት በፈውስ ህክምና እንዲሁም ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በህክምና ትምህርት መስክ እውቅናን ያተረፈው የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ (ኦቶና) ሆስፒታል አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት ወደ ኮምፕሬሄንሲፍ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (Comprehensive Specialized Hospital) ደረጃ ማደጉን በዛሬው እለት ተገልጿል።
ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ የጤና ሙያ የተወጣጡ እንስፔክሽን ቡድን አባላት የሆስፒታሉን አጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ እና ቀጣይ የተያዙ እቅዶችን ከገመገሙ በኋላ ይህ እውቅና መሰጠቱን የሆስፒታሉ አስተዳደር አሳውቋል።
ውድ የሆስፒታላችን ተገልጋዬች እንዲሁም አጠቃላይ የዎላይታና አካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አለን ሲል የዩንቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ዳይሮቶሬት ዘግቧል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡Wolaita Timese/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw…
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 12/01/14 E.C , Sodo, #Ethiopia🇪🇹
