የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች አቅመ ደካማ ወገኖችን እንኳን አደረሳችሁ በማለት ምሳውን በጋራ ተመግበዋል።
በቦታው የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ ለተጋባዦች የዎላይታ ሕዝብ ዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ ያለው ለለሌው በማካፈል በአንድነት የሚያከብሩት የእርቅና የፍቅር በዓል በመሆኑ ያንን ለማሳየት ከእናንተ ጋር ምሳ ለመብላት ፈልገናል በማለት እንኳን አደረሳችው የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከአቅመ ደካሞች ጋር በእንዲህ አይነት ሁኔታ በዓሉን ማክበር በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ሁሉም የዞን ህብረተሰብ በዓሉን ሲናከብር አቅም ላጡት በማካፈል መሆን እንዳለበት ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።
በዓሉ የሠላም፣ የደስታ ፣የጤና እና የብልጽግና እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።
እንደ ዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘገባ ከተጋባዦች አንዳንዶቹ እንዳሉት የዞኑ አስተዳደር በበዓል ቀን አስታውሶ ይህን የመሰለ ፍቅር ስላሳየን ደስታ ተሰምቶናል በማለት ለዞኑ አስተዳደር እና ለመላው የዎላይታ ሕዝብ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።


