በሆስፒታሉ ህክምና ባለሙያዎች ላይ የተወሰደው ጅምላ እስር ሃኪሞቹ ለበርካታ ወራት የሰሩበት የቆየ ውዝፍ ገንዘብ ጥያቄ ለማፈንና በመሸማቀቅ እንዳይጠይቁ ታስቦቦበት የተደረገ ድርጊት ስለመሆኑ ከተለያዩ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩን ከታማኝ ምንጮች ባረጋገጠው መሠረት የቦዲቲ መጀመሪያ ደረጃ የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች እንደ ደንብና መመሪያው መሠረት የሠሩበትን ክፍያ ሳይሸራረፍ እና ሳይቆራረጥ ሕጉ በሠሩበት ወር እንዲከፈላቸው ቢያስገድድም አሠሪው “በጀት የለኝም በሚል እና ለመክፈል አቅም የለኝም” በሚል ክፍያውን ሳይከፍል 1 አመት የተጠጋ ያህል ጊዜ መቆየቱን ገልጿል።

የጤና ባለሙያዎችም የይከፈለን ጥያቂያቸውን ሲያቀርቡ የከተማው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ምላሽ “ይከፈላል እየሰራችሁ ጠይቁ” ከማለት ውጪ የአንድ ወር ክፊያ ሳይከፈል እየተወዘፈ 11 ወራት ይቆጠርና ባለሙያው ሥራውን እናዳይሠራ ከራሱ የተለያዩ ወጪዎችን ከራሱ ሲሸፍን “ከዛሬ ነገ ይከፈለናል” በሚል ተስፋ ሲጠብቅ በተደጋጋሚ በተዋረድ እስከ ዞን አስተዳደር ድረስ ቢጠይቁም መፍትሔ አጥተው በፍርድቤት የክስ ቻርጅ ይከፍታሉ፤ ፍርድ ቤቱም አሠሪው ውዝፍ እንዲከፍል የውሳኔ ብይን መስጠቱን አንድ ስሙን መግለፅ ያልፈለገ በሆስፒታሉ የሚሰራ ጤና ባለሙያ ተናግሯል።

ይሄው ባለሙያ ባለፈው አርብ ዕለት የሆስፒታሉ 3 የህክምና ዶክተሮችና ሌሎች ሰራተኞች እስር በተመለከተ ሲያብራራ የ11 ወራት ውዝፍ ገንዘብ ስላልተከፈለ የትርፍ ሰዓት ሥራ መሥራትን ያቆሙት ከአራት ወር በፊት እንደሆና በእነዚህ ወራት ሕብረተሰቡ ሲሰቃይ ሆስፒታሉ ተዘግቶ አንድ ቀን የከተማው ካንቲባም ሆነ ሌሎችም ሥራ አስፈጻሚ አመራሮች የሆስፒታሉ ሥራ እንዲቀጥል ያደረጉት ጥረት እንዳልነበረ አስረድቷል።

በዚህ ሁኔታ ከህክምና ባለሙያዎች ጋር ቅሬታ ውስጥ የገቡት የከተማው አመራሮችና ማኔጅመንት አባላት እንዴት የጤና ባለሙያዎችን “በማስፈራራት ወደሥራው እንመልስ” በሚል ወጥመድ አዘጋጅተው በቀን 24/4/2016 ዓ.ም ምሽት ግን የድንገተኛ ቀዶ ህክምና ባለሙያ ቀን ሥራ ላይ ውለው ማታ በመኖሪያ ቤታቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በማረፍ ላይ እያሉ ከምሽቱ 7:00 አካባቢ ለሕክምና የመጡ ባማስመሰል እስከ መኖሪያው ቤት ድረስ በመሄድ ጭቅጭቅ

ከታካሚው ጋር የመጡ አስታማሚዎች ብቻ ሳይሆን ሌሎችም በቡድን ተደራጅተዉ ወደ ባለሙያው መኖሪያ ቤት ድረስ በመሄድ ቤቱን በመክበብ “ና ዉጣና አክም” የምል ቃላትን ያሰማሉ፥ ቤቱን በኃይል ይደበድባሉ ያስፈራሩት ጀመሩ በዚህም መሀል የተረበሹት የዶክተሩ ቤተሰብና ሕጻናት ቤት ውስጥ መጮህ ይጀምራሉ፤ “ና ውጣ አለዚያ እንገላሃለን” እያሉ በሩን እየደበደቡ ሰዎቹ እቤቱ ጣሪያው ላይ የድንጋዩን እሩምታ ማውረድ ይጀምራሉ” ሐኪሙ “እኔ ተረኛ አይደለሁም ተረኞች አሉ እነሱ ጋር ሂዱ” ቢላቸውም አልተው ሲሉ ባለሙያ በዚህ መሀል ለህይወቱ በመስጋት ቤቱን ሳይከፍት ሰው ላይ ሳይሆን እቤቱ ጣሪያው ወደ ሰማይ ሽጉጥ መተኮሱን የአይን እማኝ ሁኔታውን አብራርቷል።

እንደ ሌላ አይን እማኝ ገለፃ በዚህ መሀል ተዳንግጦ ነገሩን ለማርገብ እና ለመገላገል ጎረቤት ሐኪም ይደርሳል ሰዎቹ በያዙት ዱላ ደብድበውት እርሱም ነፍሱን ለማትረፍ ሲል ወደቤቱ እሮጦ ገባ ይህ ሁሉ የሚሆነው ታካሚዋ ለሕክምና በመጣችበት ሰዓት ሕክምናው በሚሰጥበት ቦታ የሚያክሙ ሌሎች ባለሙያዎች እንደነበሩ በማስረዳት በልዩ ተልዕኮ ካልሆነ በስተቀር የሐኪሞች መኖሪያ ድረስ አስታማሚዎች መላክም መሄድም አይጠበቅም ሐኪሙ ቢፈለግ እንኳን መጠራት የነበረው ወይ በጥበቃ ወይ በመሚመለከተው አካል ነው መጠራት አለበት ስሉ የግል አስተያየት ሰጥቷል።

መብታቸውን የጠየቁ የሆስፒታሉ ህክምና ባለሙያዎች ላይ የተወሰደው ጅምላ እስር ሃኪሞቹ ለበርካታ ወራት የሰሩበት የቆየ ውዝፍ ገንዘብ ጥያቄ ለማፈንና በመሸማቀቅ እንዳይጠይቁ ታስቦቦበት የተደረገ ድርጊት ስለሆነ እነኝህ ሐኪሞች በአሁኑ ሰዓት ምንም ባልሠሩት ወንጀል የዋስትና መብታቸው ጭምር ተከልክለው እየተሰቃዩ ነው፤ የሚመለከታችሁ ባለድርሻ አካላት ነገሩን በማጣራት መፍትሔ ሀሳብ እንዲሰጡ ጠይቋል።

ጉዳዩን ለማጣራት ከከተማ አስተዳደርና ከሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ቢሆንም ካገኘን እንመለስበታለን። በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *