እጂግ አስደንጋጭና አስቸኳይ መረጃ❗️

በዎላይታ ዞን በአንድ ወረዳ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ከ100 በላይ ሰዎች በወባ ወረርሽኝ በሽታ ህይወታቸው አልፏል።

በዞኑ በኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሼላ ቀበሌ ብቻ የወባ ህመም ምልክት ታይቶባቸው ምርመራ ከተደረገላቸው 869 ሰዎች መካከል በ680 ሰዎች ላይ የወባ በሽታ መገኘቱን የጤና ባለሙያዎች የተናገሩ ሲሆን በየቀኑ በዚሁ ወረርሽኝ የሚያዙና የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር አሳሳቢ ደረጃ መድረሱንም አክለዋል።

አንድ በወረዳው ሀላሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰራ የህክምና ዶክተር “በአሁኑ ወቅት በክንዶ ዲዳዬ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በዎላይታ ዞን ባሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መስረታዊ የሚባሉ የህክምና ቁሳቁስ ባለመኖሩ የብዙ እናቶችና ህፃናት ህይወት ማዳን እየተቻለ እየሞቱ ነው” ስል ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም በዎላይታ የህብረተሰቡን ጤና “አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር” በሚል በመቶ ሚሊዮኖች ከዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች የሚመደበው ገንዘብ ለፓለቲካ ስራዎችና በአመራሮች ተከፋፍለው በማለቁ በዞኑ የወባ፣ የኩፍኝ እና ሌሎች የወረርሽኝ በሽታዎችን መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ እያደረገና በርካቶች እንዲሞቱ እያደረገ ስለመሆኑ በዎላይታ ዞን በተለያዩ መንግስት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

ለአብነትም በዞኑ በክንዶ ድዳዬ፣ ገሱባ፣ ባሌ፣ በቦሎሶና ቢጣና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የእናቶችንና የህፃናት ህይወት ለማዳን ቀላል የሚባሉ የህክምና ቁሳቁስ እንኳን ባለመኖሩ የተከሰተውን የወባና የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ማትረፍ እየተቻለ ሞት እየተከሰተ መሆኑንም ስማቸው ከተገለፀ የተለያዩ ጫናዎች ይደርስብናል ያሉ ዶክተሮች አክለው ገልጸዋል።

በተጨማርም እንደ ጤና ባለሙያዎች ገለፃ በዞኑ በአብዛኛው ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ላይ የትርፍ ጊዜ ክፍያ ለረጅም ጊዜ ባለመከፈሉ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ ከማድረጉ በተጨማሪ ከዞን ባለሙያዎች ጭምር ወረርሽኝ ወደተከሰተበት አከባቢ ለመሄድ የተመደበው ገንዘብ ለሌላ አላማ በመዋሉ ሁኔታዎችን አስቸጋሪ እያደረገ እንደሆነም በዞኑ በተለያዩ መንግስት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

እንደ ባለሙያው ገለፃ በበሽታው የተጠቁ ግለሰቦችን ለማከም የሚያስችል መድሀኒት በየጤና ተቋማት አለመገኘቱ እንዲሁም በበሽታው የተጠቁ ግለሰቦች በየቤታቸው የሚገኙ ስላሉ ወረርሽኑን ለመቆጣጠር ፈተና መሆኑን አስረድቷል።

ወረርሽኑ በአሁኑ ወቅት ያለበት ደረጃ በተለያዩ ወረዳዎች ከፍተኛ ቢሆንም “የጤና ዘርፍ አመራሮች ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው የተከሰተው ወረርሽኝ መረጃ ይፋ ከሆነ የአከባቢው ገፅታ ያበላሻል” በሚል ወደ ክልል ሆነ ወደ ፈደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሪፓርት ባለመደረጉ የሰው ህይወት እንዲያልፍ እያደረገ ስለመሆኑም አክለው ገልጿል።

የህክምና ባለሙያዎቹ በጤና ተቋማት ያለውን ተጨባጭ ችግር ማውራት፣ የትርፍ ጊዜ ክፍያ መጠየቅ እንዲሁም የትኛውም አይነት የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት በየትኛውም መንገድ ማጋለጥ ከሰራ የሚያስባርር እንዲሁም የተለያዩ ጫናዎች እንዲደርስባቸው የሚያደርግ ነው” ሲሉ አስረድቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ በሼላ፣ ሳዴ እና ሼላ መቄራ ቀበሌያት አከባቢ ብቻ ከህዳር 01 2016 ዓ.ም ጀምሮ በወባ ወረርሽኝ ምክነያት ለሞቱ ሰዎች ከአንድ መቶ በላይ ሲሆኑ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለጊዜው ባገኘው መረጃ መሠረት የሟቾች ዝርዝር

ተ.ቁ የሟች ስም👇 ቀበሌ👇

 1. ድምባቤ ሄራኖ ይናፌ
 2. ኤፍሬም ቡሩንዶ “
  3 ደስታነሽ ጰጥሮ “
 3. እስታትክ ሹምቡሎ “
  5 የጴጥሮስ መኩሪያ ልጅ “
 4. አሳሌ ጋጋ ጨሌ
 5. አርባ ሹርኬ “
 6. የአርባ ሹርኬ እናት “
 7. ደጀኔ ዳናቦ ኦቴ
  10 ሹካ ኮልባዬ “
 8. የሻንቆ ቶጋ እናት ጨሌ
 9. ታፈሴ ታራፎ “
 10. የዋዱ ቶጋ ልጅ “
 11. ትርፌ አምባ ዋሳራ
 12. የቶማስ ቶማ ልጅ “
 13. የበጋሸው ሌአ 2 መንትያ ልጆች ዋሳራ
 14. ባልቻ ሻንካ ኦቴ
 15. አላሮ ሃለለ “
 16. የታፌሰ ሞታ እናት “
 17. ጥልቄ ሀጥዬ ጨሌ
 18. ዳታ ደግፌ ሼላ
 19. ሀንጦቴ ሀላላ “
 20. ብርሃነሽ ኦርሳንጎ “
 21. የደሳለኝ ዳራቶ ልጅ “
 22. የጰጥሮስ መኩሪያ ልጅ ይናፌ
 23. የጭማ ሳንቦ 2 መንትያ ልጆች ዋሳራ
 24. ዘካሪያስ ባራና “
 25. የጋቢሳ ጋጃቦ እናት “
 26. ዱፓሬ ካምፈሶ ኦቴ
 27. የባይካ ባንቶራ ምስት ዋልጫዬ
 28. የብሳ ብብሶ ልጅ ጨሌ
 29. ታምራት ጋጋ እናት “
 30. አሳለ ጋጋ ጨሌ
 31. የአበራ አሳሌ ልጅ ብትቴ
 32. ፈቃዱ ፍርካቴ ልጅ ጨሌ
 33. አልቶ አላሮ “
 34. የቦሎሼ ባልቻ ልጅ ብትቴ
 35. የአድማሱ አሻ አባት ማራ ጨሌ
 36. ዋዛ ዋላና ኦቴ
 37. የዘውደ ባይካ ልጅ ብትቴ
 38. የአገኘሁ ንጋቱ ልጅ “
 39. የቶማስ ጌታቸው አባት ግርባ
 40. ጳውሎስ አባዬ ብትቴ
 41. የዳነቸው ዳቼ ልጆ ጨሌ
 42. ኡቤ ኡንቱኬ “
 43. የባዛና አንጃጆ ምስት ጨሌ
 44. ጆባ ማሳና “
 45. የብርሃኑ ቴማ ልጅ “
 46. መስፍን አንቃሞ መቄራ
 47. የሕዝቅኤል ዋዛ እናት “
 48. የጵልጦ ባቾሬ ልጅ ይናፌ
 49. የባትሶ እናት “
 50. ቡካሻ ዳለ መቄራ
 51. ባሣ ባላንጎ “

እነኚህ ከላይ የተዘረዘሩ የሟቾች ስም በአንድ ወረዳ ብቻ በወረርሽን የሞቱ ሲሆን እስካሁን ስማቸውን ለጊዜው ያላገኘናቸው ከ100 በላይ ሰው ከአንድ ቤት ሁለት መንቲያዎች ጭምር መሞታቸውን እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች ከአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አዋቂዎችና ህፃናት በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ህክምና እየተከታተሉ እንዲሁም ወደ ጤና ተቋማት መምጣት ያልቻሉት በየቤታቸው እንዳሉ ከደረሰን መረጃ መረዳታችን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እየተመኘን በአሁኑ ወቅት በዞኑ በተለያዩ ቦታዎች በወረርሽኙ ምክንያት እየተሰቃዩ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጂት፣ ሚዲያዎችና ጉዳዩ የሚመለከተው ሁሉ በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን። በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ቤታሎ የተጠናቀረ ዘገባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *