በዎላይታ ዞን አዋሳኝ ሃዲያ ሾኔ አከባቢ በተቀሰቀስ የኩፍኝ በሽታ 22 ህጻናት መሞታቸት ተገልጿል።

በማዕከላዊ ኢትጵጵያ ክልል ሃዲያ ዞን በተቀሰቀስ የኩፍኝ በሽታ በ14 ቀናት ውስጥ 22 ህጻናት መሞታቸውን የሆስፒታል ምንጭ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቋል።

በሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የላብራቶሪ ባለሙያ የሆኑት ነጋ ደሳለኝ በዞኑ የተቀሰቀሰው የኩፍኝ በሽታ በመስፋፋት ላይ መሆኑን እና ለዎላይታ ዞን አዋሳኝ አከባቢ በሾኔ ከተማ ብቻ ከ80 በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

“በታካሚዎች ብዛት እና በአልጋ እጥረት ምክንያት ሆስፒታሉ ለታማሚዎች በጊዜያዊ ድንኳኖች ውስጥ ህክምና መስጠት ጀምሯል” ሲሉም ነጋ ገልጸዋል።

በአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ላይ እንደ ነጋ ገለፃ፣ ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 12 ዓመት የሚሆኑ ህጻናት ናቸው። “ላለፉት ሁለት ሳምንታት በየቀኑ አንድ ወይም ሁለት ህጻናት በበሽታው ህይወታቸው እያለፈ ነው” በለዋል።

ሰሞኑን በዎላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሼላ ሳዴ እና ሼላ መቄራ ቀበሌያት ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች በላይ ህይወት የቀጠፈው ወባ ወረርሽኝ በሚመለከታቸው አካላት ተገቢ ትኩረት እንዲያገኝ በተደረገው ያላሰለሰ የበርካታ ሚዲያዎች ጥረት ምክንያት መረጃው የደረሳቸው የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥረት በመጀመሪያው ኢንኩቬሽን ጊዜ (በ14 ቀናት) የወባ ስርጭቱ ከፍተኛ መሻሻል የታየ ሲሆን የሰው ሞት ምጣኔም በእጅጉ መቀነሱን በዛሬው ዕለት መዘገባችን ይታወሳል። በናትናኤል ጌቾ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *