“የወጣው ደብዳቤ የዜጎችን ህገመንግስታዊ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የሚቃረን ነው”- የዎህዴግ ሊቀመንበር

የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ጎበዜ ጎኣ አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “ሰርኩላር ደብዳቤ” በሚል ለሁሉም ዞኖች የወረዳና የልዩ ወረዳ እንሁን ጥያቄን በተመለከተ በተፃፈ ደብዳቤ በሰጡት ማብራሪያ ክልሉ ይቅርታ ጠይቆ ህገመንግስታዊ ሥርዓት ተገዥ እንድሆኑ አቅጣጫ ጭምር እንድያስቀምጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀመንበሩ “የደብዳቤው መንፈስ በጥቅሉ እኔ የማስብልህ እንጂ አንተ የሚታስበው ስህተት ነው በሚል በግርድፉ የዜጎችን ዴሞክራሲያዊና ህገመንግስታዊ መብትን የሚጋፋ ተቀባይነት የለለው ደብዳቤ መሆኑን ሁሉም ሰው ልብ ይሏል” ስሉ አብራርተዋል።

አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በመባል የተደራጀው ክልል የዜጎችን ህገመንግስታዊ መብትን ለመደፍጠጥ የተሰጠው አንዳች ህጋዊም ሆነ ህገመንግስታዊ መብት የለለውና ዜጎች በፈለጉት ጊዜ የፈለጉትን አደረጃጀት ፈጥሮ የመኖር መብታቸውን የኢፌዴሪ ህገመንግስት የሚያረጋግጥ በመሆኑ በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 9 መሠረት የክልሉ ሰርኩላር ደብዳቤ ተቀባይነት የለለው መሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንድወሰድ አቶ ጎበዜ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በሰጡት አጭር መግለጫ አሳስበዋል።

በመጨረሻም በዎላይታ ውስጥ የወረዳና የልዩ ወረዳ እንሁን የሚል ጥያቄ ባይኖርም የትኛውም አከባቢ ያለ ህገመንግስታዊ ጥያቄ የሚያነሳ ህዝብ በአግባቡ ልደመጥና ልሰማ እንዲሁም ህገመንግስታዊ ጥያቄው ጊዜ ሳይወስድ ምላሽ ልሰጠው የሚገባ ጉዳይ በመሆኑ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ የዜጎችን ህገመንግስታዊ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የሚቃረን በመሆኑና በሀገርቱ የበላይ ህግ የሆነውን ህገመንግስት ጋር የሚጣረስ ስለሆነ ደብዳቤው በደብዳቤ ተሽሮ ዛሬ ነገ ሳይባል የማሻሻያ ሀሳብ ለሁሉም ዞኖች እንድቀርብም የዎህዴግ ሊቀመንበር ጠይቀዋል።

“ነፃነት የተፈጥሮ መብት ነውና የተፃፈው ደብዳቤ ስህተት ስለመሆኑ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የክልሉን ህዝቦች ይቅርታ ጠይቆ የመንግሥትና የህዝብ ኃላፊነት የተሸከሙ ሰዎች ለህግና ህገመንግስታዊ ሥርዓት ተገዥ እንድሆኑ አቅጣጫ ጭምር እንድያስቀምጥ” ሲሉም አቶ ጎበዜ በጥብቅ አሳስበዋል። በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *