በዎላይታ ሶዶ ከተማ ሀሰተኛ ደረሰኝ በመጠቀም ቤቷ ተሽጦ ከእነ ልጇ ጎዳና የወጣች ሴት ፍትህ

በከተማዋ ተጠርጥረው ባሳተመው ሐሰተኛ ደረሰኝና እሱ በሰራው ማጭበርበር ቤቷ በሕገወጥ መንገድ በባለቤቷ ተሽጦባት ልጇን ይዛ ከቤቷ ተባርራ በሜዳ የሚትንከራተት እናት “ፍትህ ወደየት ነው” በሚል ለፈጣሪ፣ ለመንግስትና ለህዝብ ሁኔታውን በእምባ ታሰርዳለች።

ባለፈው ሳምንት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ድል በገሬራ ቀበሌ አቶ ተስፋሁን በለጠ ( የአማራር ወንድም ) የተባለ ግለሰብ የሕገወጥ ደረሰኝ አመሳስሎ በማሳተም የቤት ሽያጭ ውል ማጽደቂያ በአራዳ ቀበሌ ገቢዎች የተከፈለ በማስመሰል ባለቤቱ ( ወይዘሮ ቤተልሔም ለማ ) ሳታውቅ ቤት ለመሸጥ የሰራው ሀሰተኛ ደረሰኝ ስለመሆኑ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት በማረጋገጥ ያወጣው ዘገባ ተከትሎ ተጠርጣሪው ታስሮ የፍርድ ሂደት እንዲከታተል ተደርጎ ነበር።

ነገር ግን አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ሀሰተኛ ደረሰኝ በማሳተም የፈጸመው ወንጀል ሳያንስ ባለቤቱ ሳታውቅ ቤት ለግለሰቦች በመሸጥ ከቤቷ በባዶ እጅ ወደ ጎዳና እንድትወጣ ያደረገው ግለሰብ በዞኑ የአንድ መምሪያ ኃላፊ ወንድም ተገን በማድረግ ዋስትና የማያሰጥ ከባድ ወንጀል ቢሆንም የፍርድቤት ቀጠሮ እንኳን ሳይደርስ ከእስር መለቀቁን ከተበዳይ ወገን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የዞን አቃቤ ሕግ ሙሉ መረጃ ደርሶበት ክስ ከመሰረተ በኃላ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መጥሪያ ወጥቶለት ተጠርጣሪው በሶዶ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት እየሰራ ባለበት አሁን ያለው የዞን አመራሮችና የሶዶ ከተማ አስተባባሪዎች ጭምር ተሰብስበው የተነጋገሩ ቢሆንም “ጉዳዩ ይፋ ከወጣ በዘርፉ የተፈፀሙ በርካታ ጥፋቶች ይጋለጣሉ” በሚል በመፍራት ግለሰቡ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ ተደርጎ ቢቆይም ባለፈው ሳምንት ያወጣነውን ዘገባ ተከትሎ ተጠርጣሪው በፓሊስ ጣቢያ ሆኖ የፍርድ ሂደት እንዲከታተል ቢደረግም በጫና በድጋሚ እንዲፈታ መደረጉንም ከምንጮቻችን አረጋግጠናል።

አንድ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ የሚገኝና ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ ግለሰብ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እንደገለፀው “የዞኑ የገቢዎች ኃላፊ ሆኖ የእሱ ወንድም ሐሰተኛ ደረሰኝ በማሳተም በከተማ ውስጥ ከፍተኛ የመንግስት ገቢ እንዲሰወር ብቻ ሴይሆን ከባለቤቱ በመደበቅ ቤቷን ሽጦ ጎዳና እንዲትወጣ እንዲሁም ተመሳሳይ ድርጊት በሌሎች ላይም እንደፈፀም ባደረገው ተጠርጣሪ ላይ ፖሊስ ምርመራ ካደረገ በኃላ ሙሉ መረጃ አሰባስቦ በከባድ ወንጀል ክስ እንዲመሰረት ለዞኑ አቃቤ ሕግ ቢቀርብም ክስ እንዳይመሰረት ጫና የፈጠረ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ዘገባ እናንተ ከሰራችሁ በኃላ አቃቤ ሕጉ ደንግጠው ዋስትና በሚከለክል ከባድ ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ በፓሊስ ጣቢያ ሆኖ የፍርድ ሂደት እንዲከታተል ቢደረግም በጫና ከእስር እንዲወጣ መደረጉ ለህገወጥ ተግባር ሽፋን እንደመስጠት ነው” ሲል አስረድተዋል።

በዚህ ሁሉ መሀል ተጠርጥረው ባሳተመው ሐሰተኛ ደረሰኝና እሱ በሰራው ማጭበርበር ቤቷ በሕገወጥ መንገድ ተሽጦባት ልጇን ይዛ ከቤቷ ተባርራ በሜዳ የሚትንከራተት እናት “ፍትህ ወደየት ነው” በሚል ለፈጣሪ፣ ለመንግስትና ለህዝብ ሁኔታውን በእምባ ጥሪ እያቀረበች ነው።

በአከባቢው የሚገኙ የፍትህ ተቋማት ይህንንና መሰል ወንጀለኞችን ተከታትሎ ወደ ሕግ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን፤ ይህ ሳይሆን ስቅርና ለሚፈጸመው ወንጀል የመንግስት አመራር ሽፋን እየሰጠ የሚቀጥል ከሆነ ስርዓት አልበኝነት ይነግሳል” በሚል በርካቶች እየጠየቁ ሲሆን እኛም ለበርካቶች ትምህርት እንዲሆን በማሰብ ከላይ ያቀረብነው ጉዳይ የደረሰበትን ተከታትለን እንደምናቀርብ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *