በአንድ ቀን 3 የዲስፕሊን ጥሪ ደብደቤ ተፅፈው ግለሰቡ ጋር ሳይደርስ ከኃላፊነትና ከስራ እንዲታገድ መደረጉ አነጋጋሪ ሆነ።

የአርሶአደሩን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የተቋቋመው የዎላይታ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን “ከዓላማው ውጪ የሌቦች መሸጋገሪያና ዋሻ እየሆነ ነው” ሲሉ የዩኒየኑ ባለድርሻ አካላት ቅሬታ አቅርቧል።

አንድ ስሙን መጥቀስ ያልፈለገው የዩኒየኑ ባለድርሻ እንደገለፀው ሌብነትና ዝርፊያ ለማስቆም ባደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትግል በአደረጃጀት የዩኒየኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ዳሳና ዋና ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአሰራር ጥሰት በመፈጸም በአንድ ቀን ሶስት የዲስፕሊን ጥሪ ደብደቤ በድብቅ መዝገብ ቤት ተደራጅቶ የጥሪ ደብዳቤ ግለሰቡ ጋር ሳይደርስ ያለምንም ጥፋት ከመደበኛ ሥራ የማፈናቀል እርምጃ እንደተወሰደበት እንደማሳያነት ገልጿል።

ከአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ህግ መሠረት በህጋዊ ተቀጣሪ ሠራተኛ ላይ የሥራ እገዳ ይቀድማል ወይስ የዲስፕሊን ክስ ይቀድማል ? በሚለው መነሻ አካሄዱ ህጋዊ አሰራር የጣሰ ስለመሆኑም በጉዳዩ ዙሪያ ተጠይቆ አንድ የህግ ባለሙያ አስረድቷል።

አክለውም የህግ ባለሙያው ከሥራ ማፈናቀል ይቀድማል ወይስ የዲስፕሊን ክስ የጥሪ ደብዳቤ ይቀድማል ? እንግዲህ ከታች የሚትመለከቱት ሶስት/3/ የተለያዩ የጥሪ ደብዳቤ ግን በአንድ ቀን ተዘጋጅቶ ታይቶ የማይታወቅ እና መሰል ጥሰቶችን ፈጽሞ ካለምንም ጥፋት ሠራተኛ ከመደበኛ ሥራ ማፈናቀል የዩኒየኑ ስም የሚያጎድፍ እና ህገወጥ ተግባር ስለመሆኑም ጠቁሟል።

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ በኅብረት ሥራ ማህበራት በሰዉ ኃይል አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 2/2005 መሠረት ከሳሽ አቶ ዳሳና ዋና ጉዳዩን በዎላይታ ዞን ከፋተኛ ፋ/ቤት በጠበቆቻቸው በኩል እየተከታተለ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመላከተ ሲሆን ከሳሽ የሰዉ እና የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል፥ በጉዳዩ ዙሪያ የዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን የያዘ ሲሆን ዉጤቱን በጋራ የሚናየዉ ይሆናል።

ከዎላይታ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን ለዞኑ መሠረታዊ ፍጆታ ስኳር እያቀረበ የነበረውን በወቅቱ በተፈጠረዉ ችግር መነሻ ተብሎ ግልጽና አሳማኝ ሁኔታ ሳይፈጠር በደብዳቤ ብቻ ዉል ማቋረጥና ለሌላ ማስተላለፍ ተገቢ አይደለም በሚል መከራከሪያ በማቅረቡ የዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ የነበረው ከኃላፊነታቸው እንዲነሳ ከተደረገ በኃላ ከሌሎች ግብረአበሮቻቸው ጋር በመናበብ ለህብረተሰቡ የመጣውን ለግል ጥቅም ማዋላቸው በመረጃ መጋለጡን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ሌላው በቅርቡ ለዎላይታ ሶዶ ዱቀት ፋብሪካ “ስራ ለማስጀመርና ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር” በሚል ከወራት በፊት ከዎላይታ ዞን አስተዳደር ቀጥታ ለስንዴ ግዢ ከሶስት ሚሊየን ብር በላይ ተመድበው በዎላይታ ገበሬዎች ዩኒየን በኩል ከተገዛ በኋላ በሶዶ ከተማ አንድ ፋይናንስ ባለሙያ አማካይነት ወጪ ሆኖ እንዲረከብ የተደረገ ቢሆንም ስንዴው የት እንደገባ አለመታወቁን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በተለይም ዩኒየኑ በርካታ መሠል ግዢዎች እንዲከናወኑ ሁኔታዎችን በማምቻቸት ከአመራሮችና ከጥቂት ባለሀብቶች ጋር በመመሳጠር የአርሶአደሩን ህይወት ለመቀየር ከተቋቋመበት አንገብጋቢ ዓላማ ውጪ ህገወጥ ተግባር ላይ መሰማራቱንም ከደረሱን ተጨባጭ መረጃዎችና ሰነዶች ማረጋገጥ ችለናል።

በተጨማሪም በአከባቢው በየወሩ መንግስት የህብረተሰቡን ኑሮ ሁኔታ ለማቃለል ተብሎ የሚቀርበው ዘይትና ስኳር እንዲሁም ሌሎች የፍጆታ እቃዎች፣ ማዳበሪያ የመሳሰሉትን የሚመለከታቸው አካላት ተገቢ የሆነ ክትትል፣ ቁጥጥርና ህጋዊ ተጠያቂነት ባለመኖሩ በህገ ወጥ መንገድ በግለሰቦች እጅ መግባቱን በዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ለዞኑ ኅብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት በጻፈዉ ደብዳቤ መነሻ ጦና ሸማቾች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኦዲት ተደርጎ ወደ መቶ ኩ/ል የሚጠጋ ስኳር በዩኒየኑ በህገወጥ መንገድ በዘረጉት መስመር መበላቱ ተረጋግጦ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠቅላላ ጉባኤው ዉሳኔ የተሰጠ ብሆንም የዞኑ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ሆነ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እስካሁን ዝምታ መምረጣቸውን ተገቢ እንዳልሆነ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *