በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደረጃጀት ሂደትን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያጭበረበሩ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

የቀድሞ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ሕዝቦች ክልል የአደረጃጀት ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ በሚደረግ የሽግግር እንቅቃሴ ውስጥ መላው የመንግስት እና የሕዝብ አደረጃጀቶች ለዚሁ ሥራ ትኩረት መሰጠቱን እንደ ምቹ ሁኔታ የቆጠሩ የቀድሞው ደ/ብ/ብ/ህ ክልል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቢሮ ሐላፊዎችና አመራሮች የ32 ሚሊዮን ብር ዘረፋ ማካሄዳቸው በምርመራ በመረጋገጡ ተጠርጣሪዎቹ ለህግ የማቅረብ ሥራ መጀመሩን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ታማኝ የመረጃ ምንጮች ከአርባምንጭ ገልፀውልናል።

እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ የዚሁ የሙስና ሰንሰለት በዎላይታ ዞን የመንግስትን መዋቅር ተክተው በአቤ-ልጅ ኔትወርክ፣ በአከባባዊነት ኔትወርክ፣ በትውውቅ እና በጥቅም እንዲሁም በቤተሰባዊ ኔትዎርክ ካደረገው ህቡዕ አደረጃጀት ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለው እንደሆነም የተነገረ ሲሆን ምርመራው ተጠናክረው እንደሚቀጥልም ተነግሯል።

በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *