በጎፋ ዞን አመራሮች ፎርጅድ የማይበቅል የቦቆሎ ዘር በማቅረባቸው አርሶአደሩ ለኪሳራ ያጋለጡ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ተጠይቋል።

ጎፋ ዞን በአዲሱ ደቡብ ክልል ውስጥ ካሉት 12 ዞኖች መካከል ከፍተኛ የቦቆሎ አምራች ዞን ሲሆን ዞኑ በባለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ባጋጠመው የእርጥበት እጥረት ከፍተኛ የቦቆሎ ምርት በመጥፋቱ አርሶ ከደሩ በአምራችነቱ ከሚታወቅበት ወደ ተመጽዋችነት የተቀየርበት ሁኔታ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዘንድሮ ምርት ዘመን ሁኔታዎች ተስተካክለው ለእርሻ ስራ ምቹ የሆነ የዝናብ ስርጭት በመኖሩ አርሶ አደሩ የተሻለ ምርት ለማግኘት እና በባለፉት የምርት ወቅቶች ያጣውን ምርት ለማካካስ ከፍተኛ የእርሻ ዝግጅት ያደረገበት ጊዜ እንደነበረም ተገልጿል።

አርሶ አደሩ ዘንድሮው የተሻለ ምርት ለማግኘት የግብርና ምርት ማሳደጊያ ግብዓት ለመግዛት ከድርቁ የተረፉ ከብቶችን በመሸጥ የግብርና ግብዓት እንዲቀርብለት ለግበርና ተቋም ፍላጎት ማቅረቡን ተከትሎ የቀረበው ምርጥ የቦቆሎ ዘር ከድርቁ ባልተናነሰ ሁኔታ አርሶ አደሩ እንዲከስር ምክንያት መሆኑን አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የግብርና ባለሙያ ከስፍራው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድተዋል።

ክስተቱ የተፈጠረው በዞናችን ግብርና መምሪያ የምርጥ ዘር አቅርቦትን በበላይነት የሚከታተል ስሆን በዘንድሮ ምርት ዘሜን በዞኑ ግብርና መምሪያ ተቆጣጣሪነት የቀረበው ምርጥ ዘር የማይበቅል እንዲሁም ነቀዝ የበላው ሆኖ መገኘቱንም ባለሙያ ጠቁመዋል።

በሌላ መልኩ “ፓዬነር ሊሙ” የተባለ ትክክለኛ ቦቆሎ ዘር በማስመሰለ ሊሙ ምርጥ ዘር እንደ ሀገር ተፈላጊ እና በአካባቢያችን ይበልጥ ተፈላጊ በመሆኑ በማስመሰል ሊሙ ያልሆነ ግን ፎርጅድ ሊሙ በማሰራጨቱ አአርሶአደሩን ለክሳራ እንዲደረግ መደረጉንም አክለው ገልጸዋል።

BH140 የተባለ ምርጥ ዘር ደግሞ የነቀዘ ዘር ለአርሶአደሩ በማሰራጨቱ ዳግም በአርሶ ከደሩ ላይ በደል ተፈጽሞ ሳለ አርሶ አደሩ ለክሳራው ማካካሻ እንዲሰጠው ብጠይቅም ሰሚ በማጣቱ በቀረበው ዘር የተሸፈነው መሬት ሙበሙሉ ሳይበቅል መቅረቱንም ተናግረዋል።

አንድ በደምባ ጎፋ ወረዳ ሞዴል አርሶ አደር የሆኑት ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ “ጉዳዩን በአቅራቢያው ላለው ግብርና ተቋም አቤቱታ በተደጋጋሚ ያቀረበ ስሆን ምርጥ ዘር የተባለው የቀረበው በዞኑ ግብርና መምሪያ በኩል በመሆኑ የወረዳ ግብርና ተቋም ጥያቀውን ለዞኑ ግብርና መምሪያ አሳውቀናል” ከማለት ያለፈ ምላሽ መስጠት እንዳልተቻለም ገልጸዋል።

በዚህ ጉዳይ የዞኑ ግብርና መምሪያ ለአርሶ አደሩ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጉዳዩን ለማጥፋትና ለማፈን ጥረት እያደረገ ያለ በመሆኑ የአርሶ አደሩን ጩሄት የሚሰማ የጠፋ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ምላሽ በመስጠት ከድርቁ የተረፉ ከብቶችን በመሸጥ የግብርና ግብዓት እንዲቀርብለት ገንዘብ ቢሰጡም ፎርጅድ ዘር በማቅረብ ለክሳራ ያደረጉት ተጠያቂ እንዲሆኑ አርሶአደሮቹ ጥሪ አቅርቧል።

በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *