የትኛውም ቃል (ስም) የፊደል አፃፃፍ ከባለ ቋንቋ/ተናጋሪው (Native speaker) በሌላ ፊደል ገበታ ተቀይሮ በጥሬው ሲፃፍ Original አጠራሩን (Pronunciation) ሳይለቅ መፃፍ እንዳለበትና በተቃራኒው መፃፍ ደግሞ ቋንቋ እንዲሞት፥ ዋና ትርጉሙ እንዲጠፋ ማድረግ በመሆኑ መቀየር እንደሌለበት በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ያብራራሉ።

በትናንትናው ዕለት ከታች በምስሉ የምንመለከተው የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት አጥር ዲዛይን ከመሰራቱ በፊት ከህዝብ አስታያየት ለመቀበል ለትችት ያቀረበውን በተመለከተ ለዘርፉ ባለሙያዎች መተው በፅሑፉ ላይ የተወሰነ መሠረታዊ የሆነ ሀሳብ እናንሳ።

በማወቅ ሆነ ባለማወቅ የህዝብ ተቋም የሆነም ጭምር የህዝብን (የብሄሩን) ስም (ፊደል) በትክክል እየፃፉ እንዳይደለ የዘርፉ ባለሙያዎች ያረጋግጣሉ። ለዚሁም ትክክለኛ አፃፃፍ ዎላይታ (Wolaita) ስለመሆኑ በብሄሩ ተወላጆች በተለያየ ጊዜ የተፃፉ መፅሐፎችን ማየት በቂ ነው። ለምሳሌ “ከለምለምቷ ዎላይታ መፅሐፍ እስከ የዎላይታ ህዝብ ታሪክ” ከእነ አቶ አብራሃም ባባንቶ እስከ አቶ ዋና ዋጌሾ ጨምረው አቶ ዋዱ ዳና፣ አምሳሉ መሠኔ፣ አማኑኤል አብራሃም፣ አብራሃም ባቾሬ እንዲሁም ለዘርፉ ቅርብ የሆኑ ደራሲያንና የታሪክ አዋቂዎች በመፃፋቸው ሆነ በተለያዩ ፅሁፎቻቸው ላይ የብሄሩን ስም ዎላይታ (Wolaita) እንጂ ወላይታ (Welaita) ብለው የፃፉበት አንድም ቦታ አለመኖሩን ለማረጋገጥ ተችሏል።

በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት የዎላይታ ዞን ህጋዊ የስራ ቋንቋ ዎላይታቶ ነው። ያንን ህግ ደግሞ የትኛውም ተቋምና ግለሰቦች ማክበር አለባቸው። ወደ ኦሮሚያ ስትሄዱ የትኛውም የተቋማት ስም ቀድሞ በኦሮሚፋ፣ ጌዲኦ ስትሄዱ ጌዶኡፋ፣ ትግራይ ትግረኛ፣ ሲዳማ ላይ ሲዳመኛ ከተፃፈ በኃላ በአማርኛ እንግሊዝኛ የሚፃፈው…….. ዎላይታ ላይ ያ የለም። የራስን ቋንቋ፣ ባህልና እሴት ማክበር ሌላውንም ማክበር ማለት አይደለም እንዴ ?

እስኪ በተነሱ ሁለት ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን👐

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *