የአንድ ከተማ ውበት ሆነ ለከተማዋ ንግድ፣ ኑሮ፣ እንቨስትመንት እንዲሁም ለቱሪዝም ዕድገትና እንቅስቃሴ የመንገድ መሠረት ልማት ምቹ መሆን ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

ሰሞኑን በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከሌዊ ሪዞርት ጀምሮ ወደ ግብርና ኮሌጅ የሚወስደው የዘመናት የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየው በበርካቶች ጥረትና ትግል መንግሥት አውንታዊ ምላሽ በመስጠቱ እንዲሰራ ወደ ተግባር ተገብቶ እንቅስቃሴ ስለመጀመሩ ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።

በአሁኑ ወቅት የመንገድ ግንባታ ሂደት በይፋ ለመጀመር መንገዱ በሚገነባበት ቦታ የሚገኙ ይዞታቸው የተለያዩ ተቋማት፣ የግለሰቦች እንዲሁም የንግድ ቤቶች የመሬት ካሳ ግመታ በአብዛኛው ቢጠናቀቅም ጥቂት የሀይማኖት ተቋማትና ንግድ ቤቶች ለዚሁ የሰፊው ህዝብ መልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ የሆነ ልማት እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ በሚመስል አካሄድ ከተለመደው ህጋዊ አሰራርና ትብብር በማፈንገጥ “ካሳም አንቀበልም፥ ከቦታውም አንነሳም” የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ተከትሎ በዛ ምክንያት ብቻ ሂደቱ እየተስተጓጐለ ስለመሆኑ አንድ የመሬት ካሳ ሂደት ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ባለሙያ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድተዋል።

የከተማ ውበት የሚለካው የመንገድ ስታንዳርድ እና ስፋት ነው፤ የትም አከባቢ ህዝባዊ ልማት ስራዎች በሚሰሩበት ወቅት በአሰራሩ መሠረት የትኛውም የተቋም ሆነ የግለሰብ መሬት ይዞታ ተገቢ ካሳ ተከፍሎ መስራት የተለመደ አሰራር መሆኑን በመግለፅ የከተማው ነዋሪዎች ለፕሮጀክቱ ስኬት በቀናነት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለበትም ባለሙያው አሳስበዋል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *