በዞኑ በቅርቡ ከኃላፊነታቸው በተነሱ አመራሮች ምትክ አዲስ የፓርቲው እና የምክትል አስተዳዳሪ እንዲሁም ረዳት የመንግስት ተጠሪ ሹመት የተሰጠ ሲሆን በዚሁም መሠረት አቶ ዘውዱ ሳሙኤል የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ በመሆን ተሹመዋል።

በተጨማሪም አቶ ጎበዘ ጎዳና የዎላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል የዎላይታ ዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የመንግስት ረዳት ተጠሪ በመሆን መሾማቸውን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *