አዲሱ ክልል ከህዝብ ፍትሃዊና ዕኩል ተጠቃሚነት አንፃር ምሁራንና የአከባቢው ነዋሪዎች ምን ይላሉ ❓

በተለይም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በቅርቡ በይፋ ከተመሠረተ ጀምሮ ከላይ በተነሳው መሠረታዊ ጥያቄ ዙሪያ አንድ የክልሉን ፓለቲካ በቅርበት የሚከታተል ምሁር ሀሳብና ምልከታ ይዘን መጥተናል።

ለዚሁ ምርመራ ዘገባችን “የአዲሱ ክልል ከህዝብ ፍትሃዊና ዕኩል ተጠቃሚነት አንፃር ምሁራንና የአከባቢው ነዋሪዎች ምን ይላሉ?” በሚለው አንድ የክልሉን ፓለቲካ በቅርበት የሚከታተል ምሁር ስንጠይቅ “ፍትሀዊ እና ተመጣጣኝ መንግስታዊና ፖለቲካዊ ዉክልና ባለማግኘቱ አንኳር በሆኑ ኢኮኖሚያዊ ሆነ ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ለማስገኘት እንዲሁም የልማት ፍትሃዊነት ለማስጠበቅ ግልፅ እና አሳታፍ የህግ ሥርዓት ተዘርግቶ እንድመራ መግባባት ተፈጥሮ መስራት ሲገባ በአሁኑ ወቅት ከዚያ እውነታ በተቃራኒው ተጨባጭ እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቁሟል።

“የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምድብ ችሎት ዎላይታ ሶዶ የተቋቋመው የፍትሕ አገልግሎቱን ለአብዛኛዉ ክልሉ ሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ በቀድሞ ክልልም አገልግሎት እየሰጠ የነበረ ቢሆንም ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ለአብዛኞቹ የዞን ተገልጋይ ሕዝብ ቅርብ በሆነ ቦታ አለመሆኑ ህብረተሰቡን ለተለያዩ እንግልት ማጋለጡን ምሁሩ እንደ ማሳያነት አስረድቷል።

ህገመንግስት ያጎናፀፈውን ጥቅም ሊጎዱ የሚችሉ ህጎች በህገ-መንግስት ጭምር እንዲካተት በማድረግ አዋጆች፤ ደንቦች እና መመሪያዎች ተዘጋጅተዉ ወደ ተግባር መገባቱን በመግለፅ ለአብነት በከልሉ በብሄረሰቦች ም/ቤት አማካይነት በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የበጄት ቀመር የማዘጋጀት፤ በሰራተኞች ምደባ እና ዝዉዉር ሰሞኑን በክልሉ ገቢዎች ቢሮ የተጀመረ በሌሎች ቢሮዎችና አሰራሮች የሚቀጥል ከሆነ በአከባቢው ኢፍትሐዊነት ሰፍኖ አደገኛ የመልካም አስተዳደርና የፓለቲካ አለመረጋጋት ምንጭ ሊሆን እንደሚችልም ምሁሩ ስጋቱን ገልጿል።

ለምሳሌ ዎላይታ ዞን “ደቡብ ኢትዮጵያ” በሚል የተዋቀረ ትንሹ ክልል ከመደራጀቱ በፊት በትልቁ ከ56 ብሄር ብሄረሰቦች በላይ አብሮ በአንድ ክልል መዋቅር በሚኖሩበት ወቅት የገዥው ፓርቲ ወይንም የመንግስት መሪነት ሚና ነበራቸው፥ በነበረው አደረጃጀት ውስጥ ከህዝብ ቁጥርና ተያያዥ እውነታ አንፃር ውክልና ተገቢ ተጠቃሚነት የነበረ ቢሆኑም አሁን ይባስ ብሎ አዝማሚያዎች በተቃራኒው እየሄዱ እንደሆነም ከዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ አብራርቷል።

የፍትሐዊነትና የዕኩልነት መርሆዎች በሚነሱበት ወቅት አንዱን የህብረሰብ ክፍል አለአግባብ በመጥቀም ሌላውን አለአግባብ የሚጎዳበት አደገኛ ሁኔታ ስለሚፈጥር የመንግስትና የሕዝብ ሀብት እንዲሁም የአስተዳደር ፖለቲካ የመምራት ኃላፊነት ተቀብለው እየሰሩ የሚገኙ አካላት የፍሐዊነትና የዕኩልነት መርሆዎችን በተገቢው ተረድተው “ለራስ በልዩነት” ከሚለው አስተሳሰብና ድርጊት ተቆጥበው በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም ህብረተሰቡ ክፍሎች የሚገባቸውን ጥቅምና ክብር መስራት እንደሚገባ አክለው ጠቁሟል።

በክልሉ ከፍተኛ ህዝብ ቁጥር ያለው፣ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ፣ ከፍተኛ የተማረ ህብረተሰብ ክፍል ያለበት እንዲሁም ከፍተኛ የንግድና እንቨስትመንት እንቅስቃሴ ያለበት፣ ለሀገራዊ ፕሮጀክት ድጋፎችና ጥሪ በሁሉም ዘርፍ ከሚገባው በላይ ሲያበረክትና እያበረከተ የሚገኘውን ህዝብ ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ ሁሉንም ህዝቦች በቅንነትና በታማንኝነት በህጋዊነት የሚገባቸውን እንዲያገኙ በማድረግ ማገልገል የነበረባቸዉ አንዳንድ ተቋማት በተቃራኒው ናቸውና ህዝቡ በፖለቲካ ሥልጣን ድልድልና በሀብት ክፍፍልም በተለይም የክልሉ ምክር ቤት በሚያውጃቸው ሀብቶች አስተዳደር ላይም ኢፍትሐዊ አሰራር ተደግሞ ለመልካም አስተዳደር ችግር ምንጭ እንዳይሆን ከወዲሁ ጥንቃቄና ክትትል ሊደረግ እንደሚገባም ምሁሩ በማጠቃለያ ሀሳቡ ጥሪ አቅርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *