በዎላይታ ዞን አስፈላጊውን መስፈርት በሟሟላት የአለም ባንክ ድጋፍ ሲያገኙ የነበሩ ሁለት ከተሞች መሰረዙ ቅሬታ መፍጠሩን ነዋሪዎች ገልጿል።

በዞኑ የአለም ባንክ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ፕሮግራም (UIIDP) ማዕቀፍ ተጠቃሚ የነበሩ ቦዲቲ እና አረካ ከተማ ከድጋፉ መሰረዛቸው በከተሞቹ ዕድገት አሉታዊ ተፅዕኖ የሚጥር ስለመሆኑ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያ ተናግረዋል።

የተጠቀሱ ሁለቱ ከተሞች ከፕሮግራሙ መሠረዛቸውን የጠቀሰው አንድ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባለሙያ መረጃ ከሆነ “የዚሁ ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩ ሁለቱ ከተሞቹም አለም ባንክ የሚጠይቀውን አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት ቢሆንም ከድጋፉ ተጠቃሚነት ስለመውጣታቸው አረጋግጧል።

እንደ ባለሙያው ገለፃ “የአረካ እና ቦዲቲ ከተሞች በ2020 አሁን ላይ አለም ባንክ ያወጣውን መስፈርት በተገቢው በማሟላትና የተሻለ አፈፃፀም በየጊዜው በማሳየት በክልሉ ከፕሮግራሙ ከፍተኛ ተጠቃሚ እየሆነ የሚገኘው ዎላይታ ሶዶ ከተማ የታለመውን አላማ ሲያሳካ የተጠቀሱ ሁለቱ ከተሞች ባላቸው አፈፃፀምና በየጊዜው በሚያሳዩት የተግባር መሻሻል መነሻ የሶዶ ከተማ ደረጃ ስለሚደርሱ ቦታውን የሚተኩ ናቸው” ተብለው ዕቅድ ተይዞ እንደነበር ገልጿል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለባለሙያው እነኚህ የተጠቀሱ ሁለቱ ከተሞች ለምንና በምን መነሻ ከአለም ባንክ ፕሮግራም ተጠቃሚነት እንደተሰረዙ ማወቅ ይቻላል ወይ በሚል ላነሳነው ጥያቄ ምላሽ ስሰጥ “ለእኛም አዲስ ነው ምክንያቱን አላወቅንም፤ በተቃራኒው መስፈርት ሳያሟሉ እንደ አዲስ የተካተቱም አሉ፦ ምናልባት ከፕሮግራሙ የተሰረዙ ከተሞች የሚመለከታቸው አካላት ለምን የሚለውን መጥቶ ሲጠይቁ ወይንም የፕሮግራሙ የበላይ አመራሮች በግብረ መልስ የሚሉትን ስንሰማ ማወቅ ይቻል ይሆናል” በሚል ጠቁሟል።

እኛም በጉዳዩ ዙሪያ ከፕሮግራሙ “ተሰርዟል” የተባሉ ከተሞች ነዋሪዎች ምን ይላሉ የሚል አስተያየት ለመጠየቅ ባደረግነው ቃለመጠየቅ “የአለም ባንክ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ተጠቃሚ የነበሩ ከተሞች ከድጋፉ መሰረዝ በከተሞቹ ዕድገት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚጥር መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ገለፃ ከተሞቹ በአሁኑ ወቅት እያሳዩ ያሉትን ዕድገትና የወደፊት እጣፈንታታቸውን የሚገታ እንዲሁም እያደገ የሚገኘውን የህብረተሰቡ መሠረት ልማት ክፍላት በማፈን በአከባቢው የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲፈጠር መነሻ ሊሆን የሚችል እርምጃ እንደሆነም አብራርተዋል።

በመጨረሻም ነዋሪዎቹ እውነትም ከተሞቹ አለአግባብ ግልፀኝነት በጎደለው ሁኔታ የተሰረዙ ከሆነ የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ያሳሰቡ ሲሆን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩን ለማጣራት የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ለማገኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ቢሆንም ተጨማሪ መረጃ ካገኘ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ እናሳስባለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *