በዎላይታ ሶዶ ከተማ የዞኑ መንግስት ለክልሉ ምስረታ ከሰበሰበው ገንዘብ ከድርሻው ባገኘው 10 ኪ.ሜ አስፋልት ለማስገንባት ያቀደው እንዳይጀመር መከልከሉ ተገልጿል።

የመንገድ ግንባታው በዎላይታ ሶዶ ከቀይ መስቀል በዩንቨርስቲ አደርጎ ዴሪ መንደር ይዞ ከገሱባ መንገድ ጋር የሚያገናኝ አምስት ኪ.ሜ አስፋልት መንገድ ግንባታ እንዲሁም ቁስቁም ማሪያም እስከ ዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ጀርባ ይዞ እሰከ ዴሪ ጋንዳባ ድረስ 5 ኪ.ሜ አጠቃላይ 10 ኪ.ሜ አስፓልት መንገድ ግንባታ የዎላይታ ዞን መንግስት ከቻይና ሁና ሆንዳ አለምአቀፍ ተቋራጭ ጋር በመነጋገርና በስራ ውል በመስማማት በራሱ በዞኑ በጀት ለማስገንባት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ በመግባት ከወር በፊት በይፋ ለማስጀመር አቅዶ የነበረ ቢሆንም እንዲቆም መደረጉን የፕሮጀክቱን ሂደት ለመከታተል የተዋቀረ ኮሚቴ አባላት መካከል አንድ አባል አስረድተዋል።

የዞኑ አስተዳደር የዚህን የከተማዋን ዕድገት የሚያፋጥን በተጨማሪም እያደገ የመጣውን የህዝብ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ በሚል ለመገንባት ያቀደው የ10 ኪ.ሜ የከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ገንዘብ ምንጩ ከክልሉ መንግስት ለሁሉም ዞኖች ከተሰጠው ክፍፍል ባገኘው ድጋፍ እንደሆነ በማስረዳት እንዲቆም የተደረገበትን ምክንያት በግልጽ ባልታወቀ ሁኔታ በክልሉ ትዕዛዝ ምክንያቱም ከዞኑ በኩል ሁሉም ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል” በሚል ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጠቁመዋል።

የክልል መንግስት ይሄንን ድጋፍ ለሁሉም ዞኖች ዕኩል ባደረጉት ተሳትፎ ልክ ክፍፍል ያደረገው በክልሉ ምስረታ ጊዜ ሁሉም ዞኖች ለምስረታው ከሚሰበሰቡት ገንዘብ 10 ፐርሰንት ለራሳቸው በመጠቀም የፈለጉትን ፕሮጀክት በራሳቸው በዞኑ ደረጃ ውሳኔ በማሳለፍ በአከባቢያቸው በውሳኔ መስራት ይችላሉ” የሚለውን የክልሉ ስራ አስፈፃሚ በወሰነው አቅጣጫ መሠረት እንደሆነም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። #WolaitaTimes

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *