ሁለት ከተሞቹ ተሰርዞ በሌሎቹ እንዲተኩ የተደረገበት “የፖለቲካ ውሳኔ ከመሆኑም በላይ ዎላይታን ለማዳከም እየተሰራ ያለ መዋቅራዊ በደል” መሆኑን ዎህዴግ ገለፀ።

የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር ለሚመለከታቸው አካላት በዛሬው ዕለት በፃፈው ቅሬታ ደብደቤ ላይ “በህዝባችን ላይ የተጀመረው ማዋቅራዊ በደል በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ስለመጠየቅ ይሆናል” በሚል በማሳሰብ ጀምሯል።

“አዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ዎላይታ ህዝብ ላይ አደገኛ ውሳኔዎች ሲወሰኑ ማየትና መስማት የተለመደ እየሆነ መጥቷል”፦ አሁን በተደራጀው አዲሱ ክልል ውስጥ 70 ከመቶ የሚይዝን ህዝብ ከፖለቲካ ውክልና፣ ከኢኮኖሚያዊ ዘርፍና ከማህበራዊ መስተጋብር ውጭ ለማድረግ በክልል ከፍተኛ አመራሮች ጭምር አቅጣጫ ተይዞ እየተሰራ ያለ አደገኛ ሥራ ባድረግነው ክትትል ልናረጋግጥ ችለናል” በሚልም ቅሬታውን በደብዳቤው ጠቁሟል።

ዎህዴግ በደብዳቤው “ሰሞኑን የአረካ ከተማንና ቦዲቲ ከተማን ከUIIDP ፕሮግራም የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመተባበር የሰረዙበት ምክንያት UIIDP ያስቀመጠውን መስፈርት ወደጎን በመተው ጂንካ ከተማንና ሳውላ ከተማን የክልል ማዕከል ከተማ ናቸው በማለት ከተሞችን ከአሰራር ውጭ ለመጥቀም ሲባል አረካና ቦዲቲ ከተማ ተሰርዞ እነርሱ እንዲተኩ የተደረገበት ምክንያት የፖለቲካ ውሳኔ ከመሆኑም በላይ ዎላይታን ለማድከም እየተሰራ ያለ መዋቅራዊ በደል መሆኑን ዎህዴግ በጽኑ ያምናል ያወግዛልም” ብሏል።

“ይህ አደገኛ ውሳኔ የእርምት እርምጃ ተወስዶ የቦዲቲ ከተማና የአረካ ከተማ በመስፈርታቸው መሠረት የሚገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ እንዲደረግ እያሳወቅን ውሳኔውም ዳግም እንዲታይልን በትህትና እንጠይቃለን” ሲልም የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር/ዎህዴግ/ ለሚመለከታቸው አካላት በዛሬው ዕለት በፃፈው ይፋዊ ደብዳቤ ገልጿል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *