የሀገር ሽማግሌዎቻችን ለሶስተኛ ወገን አቤቱታ ይዘው ከመሄዳቸው በፊት ላለፉት አመታት ከአከባቢው በሀሳብ ልዩነት ምክንያት የተራራቁ ልጆቻቸውን ያስታርቁን”

በአከባቢው “በፓለቲካ አካሄድ ልዩነት ምክንያት ብቻ ዳርና ዳር ሆነው የሚገኙ ወገኖች ወደ አንድነት፣ መደማመጥ፣ መተባበር እንዲሁም በጋራ ጉዳይ በሆኑ የህዝብ የልማት ፍላጎቶች ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡና በአንድነት በመሰለፍ በጎ ሚና ሊወጡ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ ሰብሳቢ ከየት ይምጣ?” ምላሽ አላገኘም።

እንደሚታወቀው የዎላይታ ዞን በሀገሪቱ ከየትኛውም አከባቢ በላይ ወደ 2 መቶ ሺህ የሚጠጋ ከታወቁ ከፍተኛ ዩንቨርስቲዎችና ኮሌጆች የተመረቁ የስራ አጥ ወጣቶች የሚገኙበት፤ ህፃናት በጨቅላ ዕድሜያቸው ከእናታቸው ተለይተው በሀገሪቱ ጎዳናዎች ሁሉ የስቃይ ህይወት እየገፉ የሚገኙት ፍልሰትም የችግሩ ስፋት የሚያመለክት ሲሆን በአከባቢው በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት የወጣቶች የስራ ዕድል ከፍ የሚያደርጉ እንዱስትሪና ሌሎች ተቋማት አለመኖር ችግሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ አባብሶታል።

አንድን ህዝብ ደግሞ በየትኛውም መዋቅር ላይ የሚጎዳ ውሳኔ ለመወሰን ወይንም የሚገባውን እንዳያገኝ ለማድረግ የሶስተኛ ወገን ፍላጎት የሚመነጨው እውነተኛ ህዝብ ተወካይ በውሳኔ ቦታዎች ላይ ባለማጣት እንዲሁም የህዝብ አንድነት አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ ሁኔታውን እንደ ምቹ አጋጣሚ እንደሚጠቀሙ ይነገራል።

ያ ባለመሆኑ በአከባቢው ሁለንተናዊ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥና የህዝብ መብት እንዲከበር ከፊት ሆነው ራሳቸውን ሰጥተው እየተሟገቱ እስር፣ ከስራ መፈናቀልና ስደት እያስተናገዱ የሚገኙ አብዛኞቹ ገና የኑሯቸውን መሠረት ያላስተካከሉ ወጣቶች ሲሆኑ በተቃራኒው ሁሉም ነገር የተመቻቸላቸው በየመድረኩ ከባለስጣናት ስብሰባና ዝግጅት መድረክ ፊትለፊት የማይጠፉ እነኚያ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ለምን እምብዛም የሰፊው ህዝብ ጥቅም፣ ክብርና መብት ግድ አይላቸውም❓ለምን ልጆቻቸውን ሰብስበው አስታርቀው አስማምተው ለአንድ አላማ እንዲሰለፉ አያደርጉም❓

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባለፈው ሳምንት ይፋ ባደረገው ምርመራ ዘገባችን “የአዲሱ ክልል ከህዝብ ፍትሃዊና ዕኩል ተጠቃሚነት አንፃር ምሁራንና የአከባቢው ነዋሪዎች ምን ይላሉ?” በሚለው አንድ የክልሉን ፓለቲካ በቅርበት የሚከታተል ምሁር ስንጠይቅ “ፍትሀዊ እና ተመጣጣኝ መንግስታዊና ፖለቲካዊ ዉክልና ባለማግኘቱ አንኳር በሆኑ ኢኮኖሚያዊ ሆነ ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ለማስገኘት እንዲሁም የልማት ፍትሃዊነት ለማስጠበቅ ግልፅ እና አሳታፍ የህግ ሥርዓት ተዘርግቶ እንድመራ መግባባት ተፈጥሮ መስራት ሲገባ በአሁኑ ወቅት ከዚያ እውነታ በተቃራኒው ተጨባጭ እንቅስቃሴ መኖሩን መጠቆሙ ይታወሳል።

የፍትሐዊነትና የዕኩልነት መርሆዎች በሚነሱበት ወቅት አንዱን የህብረሰብ ክፍል አለአግባብ በመጥቀም ሌላውን አለአግባብ የሚጎዳበት አደገኛ ሁኔታ ስለሚፈጥር በክልሉ ከፍተኛ ህዝብ ቁጥር ያለው፣ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ፣ ከፍተኛ የተማረ ህብረተሰብ ክፍል ያለበት እንዲሁም ከፍተኛ የንግድና እንቨስትመንት እንቅስቃሴ ያለበት፣ ለሀገራዊ ፕሮጀክት ድጋፎችና ጥሪ በሁሉም ዘርፍ ከሚገባው በላይ ሲያበረክትና እያበረከተ የሚገኘውን ህዝብ ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ ሁሉንም ህዝቦች በቅንነትና በታማንኝነት በህጋዊነት የሚገባቸውን እንዲያገኙ በማድረግ ማገልገል የነበረባቸዉ በተቃራኒው ናቸውና ህዝቡ በፖለቲካ ሥልጣን ድልድልና በሀብት ክፍፍልም በተለይም የክልሉ ምክር ቤት በሚያውጃቸው ሀብቶች አስተዳደር ላይም ኢፍትሐዊ አሰራር ተደግሞ ለመልካም አስተዳደር ችግር ምንጭ እንዳይሆን ከወዲሁ ጥንቃቄና ክትትል ሊደረግ እንደሚገባም ምሁሩ በማጠቃለያ ሀሳቡ ጥሪ አቅርበው ነበር።

ሰሞኑን ያንን መነሻ አድርገው ይሄንን ኢፍትሐዊ አካሄድ ለፌደራል መንግስት አቤቱታ ለማቅረብ የሀገር ሽማግሌዎች እንቅስቃሴ በመጀመራቸው የክልሉ መንግስት እንዳይሄዱ እያግባባቸው ነው የሚል ሀሳብ ተከትሎ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ግለሰቦች “አንድን ህዝብ በየትኛውም መዋቅር ላይ የሚጎዳ ውሳኔ ለመወሰን ወይንም የሚገባውን እንዳያገኝ ለማድረግ የሶስተኛ ወገን ፍላጎት የሚመነጨው እውነተኛ ህዝብ ተወካይ በውሳኔ ቦታዎች ላይ ባለማጣት እንዲሁም የህዝብ አንድነት አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ ሁኔታውን እንደ ምቹ አጋጣሚ ይጠቀማሉና በአከባቢው ከዚህ በፊት በሀሳብ ልዩነት የተራራቁ ለህዝብ ጥቅምና ክብር ቅድሚያ በመስጠት በአንድነት መሰለፍ እንድንችል እንዲሁም ህዝቡ በዘላቂነት የሚገባውን እንዲያገኝ ለማድረግ ለሶስተኛ ወገን አቤቱታ ይዘው ከመሄዳቸው በፊት በአስቸኳይ ላለፉት አመታት ከአከባቢው በሀሳብ ልዩነት ምክንያት የተራራቁ ልጆቻቸውን በጉተራ ሰብስበው ያስታርቁን” በሚል አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የዎላይታ ምሁራን፣ ፓለቲከኞች፣ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም በየደረጃው ተሰምነት ያላቸው ግለሰቦች ባለፉት አመታት በዞኑ የፓለቲካ አካሄድ ልዩነት ምክንያት ብቻ ዳርና ዳር ሆነው የሚገኙ ወገኖች ወደ አንድነት፣ መደማመጥ፣ መተባበር እንዲሁም በጋራ ጉዳይ በሆኑ የህዝብ የልማት ፍላጎቶች ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡና በአንድነት በመሰለፍ ለሀገራቸውና ለአጎራባች ህዝቦች ጭምር በጎ ሚና ሊወጡ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውን ለመምከር የአዲሱ ክልል ሆነ የዞን አመራሮች እንዲሁም በአከባቢው የምንቀሳቀሱ ፓለቲካ ፓርቲዎች ይሄንን ህዝባዊ አላማ ከግብ ለማድረስ ቅንጅታዊ አሰራርና መድረክ ማመቻቸትም ለጊዜው ምላሽ አላገኘምና በያለንበት ጊዜ ሳንሰጥ ልንወያይበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑ “አከራካሪ አይመስለንም” የበርካቶች አስተያየት ነው።

Wolaita Times በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *