የዎላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ ማዕከል መልሶ ለመገንባት የተመደበው ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የት እንደገባ አለመታወቁ ተነግሯል።

ከሶስት ሳምንት በፊት “አልቋል” ተብሎ ለተጠቃሚዎች “ተላልፏል” የተባሉ 2 ሼዶች በአለም ባንክ ድጋፍ የተሰራ እንጅ የመጀመሪያው ዋናው ፕሮጀክት አካል አለመሆኑንና ዘመናዊ ገበያ ማዕከል ለመገንባት በሚል ከባለ አክሲዮኖችና ከተለያዩ አካላት የተሰበሰበው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ባለቤት ማጣቱ ቅሬታ መፍጠሩ ተገልጿል።

በወቅቱ የዚሁ ዎላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ የገበያ ቃጠሎ የተጎዱት ለማቋቋም ተብሎ ሕብረተሰቡ፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የክልሉ መንግስት 10 ሚሊዬን ደግፎ በ47 ሚሊዬን ብር በኢዳብ የተሰኘ የአለምአቀፉ ኮንስትራክሽን ኩባኒያ አማካይነት ተገጣጣሚ ሕንፃ ይገነባል ተብሎ ለቅድመ ክፊያ 21 ሚሊዮን ብር ከተከፈለ በኃላ አለመጀመሩ ትልቅ ጥያቄ መፍጠሩን የከተማዋ ነጋዴዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የገበያ ቦታውን የገበያ ነጋዴ በአክሲዮን ተደራጅቶ ለመሥራት ተብሎ ከተደራጁ አምስት መቶ ሰዎች ውስጥ ብዙዎች ባለሥልጣናት በዘመዶቻቸው ስም እንደገባና ዕጣውም በ3 መቶ ሺህ ብር ሕገወጥ በሆነ ሁኔታ በገበያው ቦታ ላይ ቀድሞ የጀመሩት ሥራ ሳይጠናቀቅ መቸብቸብ ጀምሮ እንደነበር አንድ አክስዮን የገዛው ነጋዴ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያስረዳው።

ለ4ኛ ግዜ እንደተከሰተ የሚነገረውና የመርካቶ ገባያ እሳት አደጋ ስደርስ ለበዓሉ ገበያ ተብሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎች በሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ አውጥቶ ያመጣቸውን ንብረት በሙሉ አመድ ያደረገው በበዓል ዋዜማ ያጡትን ገንዘብና ንብረት እንዲሁም ድሆች እንደ አቅማቸው ሰርተው የሚተዳደሩበትን መልሰው ለመገንባት ተማሪዎች ከቀለባቸው፣ የተማሪ ወላጆች በክሳቸው ካለው፣ የመንግስት ሠራተኞች ከደመወዛቸው፣ ግል ባለሀብቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምረው የዎላይታ ህዝብ ወዳጆች ሁሉ ከያሉበት ይህ መርካቶ ገበያ ተገንብቶ ቶሎ ወደ ሥራ እንድገባ ገንዘብ ድጋፍ ያደረጉት ገንዘብም ወደየት እንደገባ እንደማይታወቅ የመረጃው ምንጭ አስረድተዋል።

በወቅቱ በተሰበሰበው ገንዘብ “ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ይገነባል ደግሞ በአራት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል” ተብሎ ብጀመርም ያለ ምክንያት ለሶስት አመታት ያህል ይገነባል እየተባለ ግንባታው ሳይጀመር “እኛ ነጋዴዎች በተስፋ ግብር ለመንግሥት እየከፈልን ነው፤ ደግሞም ያ ሁሉ ገንዘብ የት እንደገባ ሳይታወቅ ነጋዴዎች በራሳችሁ ገንዘብ የገበያ ማዕከል ለመገንባት ተደራጁ ብለውን አማራጭ ስላአጣን ተመዝግበን መዋጮ አድርገን አክሽዮን የገዛን የነበረ ቢሆንም ከሶስት ሳምንት በፊት “አልቋል” ተብሎ ለተጠቃሚዎች “ተላልፏል” የተባሉ 2 ሼዶች ማለትም አጠቃላይ ከገባያ ማዕከሉ 15 ፐርሰንት የማይሞላ ቦታ ላይ በአለም ባንክ (በUIIDP) ድጋፍ የተሰራ እንጂ ባለአክሲዮኖችና የተለያዩ አካላት እንዲገነባ ከሰጡት አለመሆኑ በአሁኑ ወቅህ የተሰበሰበው ገንዘብ ወደየት ገባ የምለውን ጥያቄ በበርካቶች ዘንድ እየፈጠረ ስለመሆኑም ጠቁሟል።

ነጋዴዎቹ አክለውም “ስለመርካቶ ጉዳይ ዝም ልል አይገባም” የፌዴራል መንግሥትም ከክልሉ ባለሥልጣናት ጀምሮ የዞን ባለሥልጣን እጅ ጠልቃ ገብቶ የሙስና ወንጀል እየፈፀሙ ያለበትን ጉዳይ ሊያጣራ እንደሚገባ እንደሚገባ እና በአስቸኳይ መፍትሔ አቅጣጫ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።

#WolaitaTimes በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *