አባ ደጀነ ሂዶቶ

አባ ደጀኔ ሂዶቶ የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሆነው መሾማቸውን ቤተክርስቲያኒቱ ይፋ አደረገች።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ አባ ደጀኔ ሂዶቶን አዲሱ “የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ” ብለው መሰየማቸውን ቫቲካን ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም.ማወጁ ተገልጿል።

አባ ደጀኔ ሂዶቶ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመንፈሳዊ እና በማህበራዊ አገልግሎታቸው የሚታወቁ ሲሆን የሀገር ስብከቱ ጳጳስ ሆነው ሲሾሙ ከአከባቢው የመጀመሪያውም እንደሆኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የዎላይታ ተወላጅ የሆኑት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህን አባ ደጀኔ ሂዶቶ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሆኖ የሾሙት ፖፕ ፍራንሲስ ሲሆኑ በዚህ የሹመት ውሳኔ ምክኒያት አባ ደጀኔ ሂዶቶ የመጀመሪያው የዎላይታ ካቶሊክ ጳጳስ ይሆናሉ ማለት ነው።

ፖፕ ፍራንሲስ የአባ ደጀኔ ሂዶቶ ሹመት ሲያፀድቁ

አባ ደጀኔ ሂዶቶ በአሁን ወቅት የሶዶ ሀገረ ስብከት ዋና ሐዋሪያዊ አስተዳዳሪ እና የቆንቶ አባ ፓስካል ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ ዲን (ዋና ኃላፊ) ሆኖ እያገለገሉ ናቸው። የክህነት አገርግሎታቸውን በዎላይታ ውስጥ በሚገኘው በታላቁ ዱቦ ሉርድ ማርያም ደብር የጀመሩት አባ ደጀኔ ከዚህ በፊት በዱቦ፥ በቆንቶ(ሶዶ)፥ በአዲስ አበባ እና በውጭ አገር በካናዳ አገልግለዋል።

የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውንም ካናዳ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ተቀብለዋል። የእሳቸው መሾም ዜና ለዎላይታ ካቶሊካውያን ትልቅ ደስታ የፈጠረ ሲሆን የታሪክ ምንጮች እንደሚገልጹት ካቶሊክ እምነት ወደ ዎላይታ አከባቢ የገባበው በ1920ቹ አከባቢ በአሁኑ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በዱቦ (አረካ) አድርጎ በታዋቂው ፈረንሳያዊ ካቶሊካዊ ካህን በአባ ፓስካል አማካኝነች ነበር።

ከእዛ ግዜ ጀምሮ በተ እምነቷ በዎላይታ አከባቢ እና በዙሪያዋ በትምህርት፥ በጤና እና በማሕበራዊ አገልግሎቶች ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተች ሲሆን በዚሁ አጋጣሚ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለአባ ደጀኔ ሂዶቶ መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

በናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *