መንግሥት ተግባራዊ ሊያደርገው የነበረው የፋይናንስ ሕግ እንደ ዳቦ ባሉ ምርቶች ላይ እስከ 16 በመቶ የሚደርስ ጭማሪን የሚያደርግ የነቀረ ሲሆን ረቂቅ ሕጉ ለአገሪቱ የተወካዮች ምክር ቤት ከተላከ በኋላ ኬንያውያን ወደ ምክር ቤቱ በማቅናት ጠንካራ የተቃውሞ ድምጻቸውን ማሰማታቸው ተከትሎ ነው ውድቅ የተደረገው።

ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም. ለማፅደቅ የታቀደው Finance Bill “እኛን የሚጎዳ ነው ሊሻሻል ይገባል” በሚል የሚቃወሙ ዜጎቿ በፓርላማው ዙሪያ ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ተጠቅሞ በፓርላማው በር ላይ የተቋውሞ ድምፅ ማሰማታቸው ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ ከፍተኛ ተደማጭነት ያለው Citizen Tv እና ሌሎች ሚዲያዎች በፓርላማ ውስጥ የሚሆነውን እና በፓርላማው በር ላይ ዜጎቹ የሚያሰሙትን የተቋውሞ ሀሳብ በእኩል ቀጥታ ስርጭት ሽፋን ሲሰጡ ነበር።

በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የሕግ ባለሙያዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተቃዋሚዎቹ ወደ ታሰሩበት አምርተው እንዲፈቱ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

እአአ 2022 ላይ ወደ ሥልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ አገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተቀባይነት እና የአገሪቱ አጠቃላይ ገቢ ጭማሪ ቢያሳይም፤ ኬንያውያን ግን ሩቶ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ኑሮ ከብዶናል በማለት ያማርራሉ።

መንግሥት ተግባራዊ ሊያደርገው የነበረው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግ ውድቅ መደረጉን የምክር ቤቱ የፋይናንስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፕሬዝዳንቱ በተገኙበት ይፋ አድርገዋል።

የፋይናንስ ኮሚቴ ሰብሳቢው ኩሪያ ኪማኒ ረቂቅ ሕጉን በተመለከተ የሕዝብ አስተያየት መሰብሰባቸውን እንዲሁም ሕጉ ተግባራዊ ቢደረግ በኬንያውያን ላይ የኑሮ ውድነት ያስከትላል በማለት ረቂቅ ሕጉ ውድቅ የተደረገበትን ምክንያት አብራርተዋል።

ይህ ረቂቅ የፋይናንስ ሕግ በዳቦ፣ በምግብ ዘይት፣ በተሸከርካሪዎች እንዲሁም በሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ ታሪፍ ላይ ጭማሪ ያደርግ ነበርእንዲሁም ብዙዎች ረቂቅ ሕጉ ተግባራዊ ቢደረግ የልጆች ዳይፐር፣ የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ፣ የኮምፒዩተር እና የሞባይል ስልኮችን ዋጋ የማይቀመስ ያደርገዋል ብለዋል።

የምክር ቤት አባሉ ኪማኒ ከውጪ በሚገቡ ምርቶች ላይ ግብሩ እንደሚጣል የተናገሩ ሲሆን ፕሬዝዳንት ሩቶ ረቂቅ ሕጉ ውድቅ ከተደረገባቸው በኋላ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። #Ethiopia #kenya

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *