በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በሚገኙ የዛይሴ ማህበረሰብ አባላት ላይ “ማንነትን መሠረት ያደረገ የዘፈቀደ እሥርና ወከባ እየተፈጸመ ይገኛል” ሲሉ ነዋሪዎችና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለፁ፡፡

የዞኑና የወረዳው የፀጥታ አባላት ሰሞኑን በሌሊት ቤት ለቤት በመዘዋወር ወጣቶች፣ ሴቶች እና ቀሳውስትን ጨምሮ 112 የማህበረሰቡ አባላትን ማሠራቸውን ነው ነዋሪዎቹና የምክር ቤቱ አባላት ለዶቼ ቬለ የተናገሩት፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የዘፈቀደ እሥርና ወከባው እየተፈጸመ የሚገኘው በወረዳው ዛይሴ ደንብሌ፣ ዛይሴ ኤልጎ እና ዛይሴ ወዘቃ በተባሉ የገጠር ቀበሌያት ውስጥ ነው፡፡

የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃፌ ቃፊሬ “እከሌ እንደዚህ ታሠረ እከሌ እንደዚህ ሆነ ብዬ የምሰጠው ምላሽ የለም“ ብለዋል፡፡

ምላሽ መስጠት ያልፈለጉበትን ምክንያት አሁንም በዶቼ ቬለ የተጠየቁት ዋና አስተዳዳሪው “ለእኛ ያልቀረበ ጥያቄ እናንተ [ ዶቼ ቬለ ] ጋር ሲመጣ መቀበል አልነበረባችሁም” ብለዋል።

አሁን እኔ መረጃውን የምሰጠው ቅሬታ አቅራቢዎቹ መጀመሪያ እኔ ጋር ቀርበው ካመለከቱ በኋላ ነው“ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *