የሙዚቃ አቀናባሪ ፈቃዱ ማንዛ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ሶዶ ከተማ መታሰሩ ተነገረ።

በዛሬው ዕለት ከንጋቱ 11:30 አካባቢ በክልሉ ፖሊስ ፓትሮል መኪና የመጡ አካላት አቀናባሪውን በዎላይታ ሶዶ ከሚገኘው ስቱዲዮ ውስጥ ያለው ንብረት ጋር ይዘው መሄዳቸውን አንድ የአይን እማኝ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።

የድምፃዊና ታዋቂ አቀናባሪ ፈቃዱ መታሰር በተመለከተ ምክንያቱን ከሚመለከታቸው አካላት ለማግኘት ለጊዜው ያልተሳካ ቢሆንም ምናልባት በቅርቡ የዛይሴ ብሄረሰብ የብሄሩን አዲስ አመት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ካደረጉ በኃላ በአከባቢው የፓለቲካ ጫና እና ማንነት ጥቃት መኖሩን ተከትሎ ከሁለት ሳምንታት በፊት እንዳይከበር ስለተከለከለው “ዮዌ ሱሩቄ” በመባል ለሚታወቅ በዓል ሙዚቃ ከማቀናበር ጋር በተያያዘ እንደሆነ ምንጮቻችን ግምታቸውን አስቀምጧል።

አቀናባሪው በተለይም በአከባቢው እንዲሁም በአጎራባች ህዝቦች ታርክ ባህልና ቋንቋን የሚያሳድጉ ስራዎችን በመስራት የሚታወቅ ስለመሆኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *