1000082472

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተባባሰ የቀጠለው የዘይሴዎች ስቃይና ሞት ከ50 ሺህ ሄክታር በላይ እርሻ ላይ የለማው የሙዝ ምርት በጥላሁን አበደና ግብረአበርቹ እየወደመ ይገኛል ይላሉ የአከባቢው ነዋሪዎች።

በሚዲያ ላይ ወጥተው ምርትና ማርታማነት ማሳደግ የሌማት ቱርፋት እያሉ ያወራሉ ህዝቡ ህገመንግስታዊ መቤቱን ስለጠየቀ ብቻ ያለማው ምርት በግፍ እንዲወድም እየተደረገ እንደሆነ WT Media በተደጋጋሚ ለማረጋገጥ ችሏል።

ህገመንግስታዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በመጠየቃቸው ብቻ የሀገር ምርት እንዲወድም ተደርጎል። አንድ ኪሎ የበሰለ ሙዝ ከ80 እስከ 100 ብር እየተሸጠ ባለበት ሀገር ላይ ምርቱ ወደ ገበያ እንዳይቀርብ መንገድ መዝጋትና አርሶአደሮች ምርታቸውን እንዳይሰበሰቡ ተደርገዋል።

ዘይሴዎች ላይ የታወጀው የዘር ማፅዳት ዘመቻ ቤትና ንብረት ማቀጠል የጤና ተቋምና ትምህርትቤት ማውደም ጨምሮ በቆሎ ሙዝ ስንዴ ምርቶችን ሰብስበው ለገበያ እያዳያቀርቡ ጭምር በማድረግ ምርቱ ባለመሰብሰቡ ምክኒያት ለከፍተኛ ውድመት ተዳርጓል።

የተሰበሰበውን ምርቶችን ማቃጠል ያልተሰበሰበውን እንዳይሰበሰብ በማድረግ በአከባቢው የተማረ ልጆች ወጣቶች እንዲሁም በሙዝ ምርት ከፍተኛ ሀብት የያዙትን ኢላማ ያደረገ የግድያና የዝሪፊያ ስራዎችን በስፋት እየሰሩ ይገኛሉ።

ዘይሴዎች የሚኖሩባቸውን ቀበሌዎች ላይ በጥላሁን ከበደ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የጋሞ ፖሊሶችና በገንዘብ የተደለሉ የክልሉ ፀጥታ አካላት ቀንና ሌሊት በአከባቢው ግድያ የንብረት ውድመትና ስቃይ እያደረሱ ይገኛሉ።

ስቃይና እንግልት ግድያ ቤት እየሰበሩ በመሸ ቁጥር በጨለማ የሚደርሰው የግድያ ቁጥር ለአይን ለማየት የሚከብድና አጠቃላይ የክልሉ መንግስት ዘይሴዎችን ከምድር ገፅ ለማጥፋት የያዙት የቆየ ሴራ አካል መሆኑን እየደረሰ ካለው ስቃይ ሞትና በከራ መረዳት እንደሚቻል ለፍሱን ነፍሳቸውን ለማዳን ወደ ጫካ የገቡት የአከባቢው ነዋሪዎች በውስጥ መስመር መረጃ አድርሰዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ዘይሴዎች ወደ ጫካ እንዲገቡ ያስገደዳቸው ለምን ህገመንግስታዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ጠየቃችሁ በሚል በቀንና በማታ ቤት እየሰበሩ እየገቡ ወጣቱን አዛውንቱን እየደገሉና ወደ ማይታወቅ አከባቢዎች እየወሰዱ ግድያ እንደሚፈፅሙ ከስፍራው አምልጦ የመጣ አንድ ወጣት ስለግድያ በነገረው መረጃ መነሻ ቤት ሆኖ ከመሞት ወጥቶ እየታገሉ መሞትን ምርጫ እንዳደረጉ ስለጉዳዩ አሳሳቢነት አንድ የአካባቢው ሰው መረጃ አድርሶልናል።

የጭካኔው ከፍታና ስቃዩን በሰሞኑ ያባባሰው አመቱን ሙሉ የሰሩትን ምርት መሰብሰብ አትችሉም በሚል በዝናብ እንዲበላሽ ማድረግና በተለይ ከ50 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ ለምቶ የበሰለውን ሙዝ ወደ ገበያ አጣወጡም ጋሞንና አመራሩን አዋርዳችሃል እናንተን ያጠገበው የበቆሎ የሙዝ የስንዴ የጤፍ ገንዘብ ነው በሚል አንድም ሰው ወደ መሬቱ ሄዶ ምንም እንዳይሰበስብ መከልከልና የተሰበሰበውን በእሳት በማጋየት የመዝ ምርቶችን ወደ ማዐሰከላዊ ገበያ የሚያደርሱ ከ200 በላይ መኪናዎች በአስቾካይ እንዲወጡ ተደርገዋል ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ከግድያ ያለፈ ንብረት ማውደምን ያካተተ መጠለያና የተከማቸ እህልን ማቃጠል ማውደም የተጎዱ ሰዎች እንዳይታከሙ ጤና ጣቢያ ላይ ያለውን መድሃኒት ጭኖ በማሸሽ እና ጤና ኬላውን ማውደም የሚበላ የሚቀመስ እንዳይኖር እህሎችን ማቃጠል ስቃይ ላይ ስቃይ ሲደራረብ ነዋሪዎች ጫካ ገብተው በረሃብና በውሃ ጥም ሲምቱ አንድም የመንግስት አካል የጠየቀ የለም ሲሉም ከተሰደዱ ሰዎች አንዱ ስለአስከፊነቱ አስረድተዋል።

ይህ ማብቂያ የሌለው የዜይሴዎችን ስቃይ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጭምር ተወካዮቻችን ያስረዱት በመሆኑ የማዕከላዊ መንግስት ቸልተኝነት እስካሁን ትርጉሙ አልገባንም ይላሉ።

ታድያ ሰው ህገመንግስታዊ ጥቃቄ በህጉ የተፃፈውን በመጠየቅ ብቻ ይህ ሁሉ ስቃይና ሞት አይገባም በሀገሪቱ ህግ ካለ ከዚህ ስቃይና የሞት ፅዋ ከመጎንጨት እንዲታደጉን የሀገሬን ህዝቦች እማፀናላሁ ሲሉም የምሬት ሰቆቃን አጋርተዋል።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media