1000082736

“ማንነታችንን መሠረት ተደርጎ የተደራጀ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደብን የሰላም ደሴቶች ነን እያሉ አይናቸውን በጨው አጥበው በአደባባይ ይዋሻሉ” ሲሉ የዘይሴ ብሄረሰብ ቅሬታ አቀረቡ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ሁሌም የሰላም ተምሳሌት በማለት የሚወድሱት የክልሉ ሰላም የት ጋር እንደሆነ የዘይሴ ወጣቶች በቁጭት እየጠየቁ መሆናቸውን WT Media ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዘይሴ ወጣቶች በአካባቢያቸው በተፈጸመው ግድያና ጭፍጨፋ ምክንያት ራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ ወደ ጫካ መግባታቸውን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ (WT Media) ገልጸዋል።

  1. የጥቃት ዘመቻው እና የጫካው ውሳኔ

ወጣቶቹ እንደሚሉት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዘይሴዎች በቀንና በሌሊት የጥላሁን ከበደ አሸባሪው ቡድን ናቸው ያሏቸው ኃይሎች ቤት በመስበር፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን፣ አዛውንቶችንና ሴቶችን እየገደሉ በመሆኑ፣ ራሳቸውን ለመታደግ ጫካ ገብተዋል።

በሚዲያ ላይ ወጥተው ምርትና ማርታማነት ማሳደግ የሌማት ቱርፋት እያሉ ያወራሉ ህዝቡ ህገመንግስታዊ መቤቱን ስለጠየቀ ብቻ ያለማው ምርት በግፍ እንዲወድም እየተደረገ እንደሆነ WT Media በተደጋጋሚ ለማረጋገጥ ችሏል።

የመንገድ መዘጋት:

በአሁኑ ሰዓት ወደ ኮንሶ፣ አርባምንጭ፣ ቡርጂ፣ ኮሬ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው። ለዚህም ዋነኛ ምክንያት የአቶ ጥላሁን ከበደ የሽብር ቡድን “ሕገመንግሥታዊ መብት ለምን ጠየቃችሁ?” በሚል ብዛት ባላቸው ኦራል መኪናዎች ወታደር ጭኖ ወደ ዘይሴ ምድር (ኤልጎ) መክተሙን ተከትሎ ወጣቶቹ ወደ ጫካ በመውጣታቸው ነው።

የግፍ መጠን:

ወጣቶቹ “ቤት ተቀምጦ በጥላሁን ሽብር ቡድን ቤት እየተሰበረ መረሸን፣ የቤት ውድ ዕቃዎች መውደም፣ የእህል ጎተራ መውደም፣ እናቶችና አባቶች ወጣቶችን ሳይለይ መገደል” ለሚፈጽመው ቡድን “ተኝቶ ከመሞት” ይልቅ ወደ ጫካ ወጥቶ ራሱን መከላከል እና መብቱን መጠየቅ እንደሚሻል አምነውበታል ይላሉ።

የጭካኔው ከፍታና ስቃዩን በሰሞኑ ያባባሰው አመቱን ሙሉ የሰሩትን ምርት መሰብሰብ አትችሉም በሚል በዝናብ እንዲበላሽ ማድረግና በተለይ ከ50 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ ለምቶ የበሰለውን ሙዝ “ወደ ገበያ አታወጡም ጋሞንና አመራሩን አዋርዳችሃል እናንተን ያጠገበው የበቆሎ የሙዝ የስንዴ የጤፍ ገንዘብ ነው” በሚል አንድም ሰው ወደ መሬቱ ሄዶ ምንም እንዳይሰበስብ መከልከልና የተሰበሰበውን በእሳት በማጋየት የመዝ ምርቶችን ወደ ማዐሰከላዊ ገበያ የሚያደርሱ ከ200 በላይ መኪናዎች በአስቾካይ እንዲወጡ ተደርገዋል ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

  1. የማንነት ጥያቄ እንደ ጥፋት ተቆጠረ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ:

የዘይሴ እና የቁጫ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገመንግሥታዊ መብት በግልጽ የተቀመጠ ቢሆንም፣ ክልሉ ይህንን ጥያቄ እንደ ጥፋት በመቁጠር እስራትና ግድያ የሚያስከትል አድርጎ መውሰዱ የሕዝቡን ቁጣ አባብሶታል።

አድልዎ:

ክልሉ አሁን ላይ ልዩ ወረዳ የነበሩትን አሌ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ፣ ቡርጂ ያሉትን ወደ ዞን ደረጃ አሳድጎ ምላሽ ሰጥቶ፣ የዘይሴን የልዩ ወረዳ ጥያቄ ለማፈን መፈለጉ የሕዝቡን ትዕግስት ገድሏል። ወጣቶቹ “እኛን የናቀ ቸልተኝነት ዋጋ ያስከፍላል” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

  1. ለፌዴራል መንግሥት የቀረበ ጥሪ

ወጣቶቹ የአቶ ጥላሁን ከበደን “የሰላም ተምሳሌት” የሚለውን የውሸት ስብከት የፌዴራል መንግሥት እውነት ወይም ውሸት መሆኑን እንዲያጣራ ጠይቀዋል።

“ለምን አይመጣም?” ወጣቶቹ በቁጭት “የፌዴራል መንግሥት የአርባምንጭ ወደ ኮንሶ ቡርጂ አማሮ መንገድ ላይ ያለውን የወጣቶችን የግፍ ግድያ ለምን ወርዶ አያይም? ለምን ሰላም ነው ብሎ በዚያ መንገድ አይመጣም?” ይላሉ።

የጦርነት ማስጠንቀቂያ:

“አሁን ላይ በዘይሴ አካባቢ ከባድ ጦርነት አለ። መከላከያውን አታለው ወደ ጦርነት እንዲገባ አድርገዋል፣ በዚህ እጅ የሚሰጥ ወጣት የለም!” ብለዋል።

የውሸት ሪፖርት ማቆም:

“ክልሉ ሰላም ነው፣ የሰላም አየር እየተነፈሰ ያለ ሞዴል ክልል ነው የምትለው የቱ ነው?” ብለው የፌዴራል መንግሥትን በውሸት ሪፖርት እያደናገረ ያለውን የክልሉን አመራር እንዲያቆም አሳስበዋል።

ዘይሴዎች ላይ የታወጀው የዘር ማፅዳት ዘመቻ ቤትና ንብረት ማቀጠል የጤና ተቋምና ትምህርትቤት ማውደም ጨምሮ በቆሎ ሙዝ ስንዴ ምርቶችን ሰብስበው ለገበያ እያዳያቀርቡ ጭምር በማድረግ ምርቱ ባለመሰብሰቡ ምክኒያት ለከፍተኛ ውድመት ተዳርጓል ይላሉ።

  1. የመፍትሔ ሐሳብ ከዘይሴ ወጣቶች

WT Media የዘይሴ ወጣቶች ለመንግሥት ይድረስልን ያሉትን የመፍትሔ መልዕክት እንደሚከተለው አቅርቧል።

የሠለጠነ ኃይል:

“እኛ የዘይሴ ወጣቶች በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተማርን ነን። በተለያዩ የሀገሪቱ የጦር መለማመጃ ቦታዎች ስልጠና ወስደን የመጣን ነን። መንግሥት ትኩረት ሊሰጠን ይገባል።”

ውይይትና መሳሪያ:

“ከመሳሪያ አኳያም በቂ መሳሪያ አለን። ከመገዳደል ፖለቲካ የክልላችን ተሿሚዎች ወጥተው ለሕዝቡ መልስ ሰጥተው፣ የጋራ ውይይት ተደርጎ ወጣቱ ከጦርነት ወደ ሥራው ይመለስ።”

የመከላከያ መውጣት እና ፍትሕ:

“መከላከያ ሠራዊት አካባቢውን ቶሎ ለቆ ይውጣ።” “እኛ ጥያቄያችን እስኪመለስ ከጫካ የትም አንሄድም። ገዳዮቻችን ለሕግ ይቅረቡ፣ ተጠያቂ ይሁኑ። ለእኛም ሕገመንግሥታዊ ጥያቄ በአጭር ጊዜ ምላሽ ይሰጠን፣ ወደ ሥራ እንመለስ።”

የዘይሴ ወጣቶች ጥሪ:

“ሰላም በሌለበት የሰላም ደሴት የሆነች ክልል እያሉ ማውራትና የውሸት ሪፖርት ማቅረብ ክልሉን ከዚህ በላይ ዋጋ ያስከፍላል። ፍትሕ ለዘይሴዎች! ሕገመንግሥታዊ ጥያቄ ምላሽ ይሰጠን!”

በተጨማሪም “ከግድያ ያለፈ ንብረት ማውደምን ያካተተ መጠለያና የተከማቸ እህልን ማቃጠል ማውደም የተጎዱ ሰዎች እንዳይታከሙ ጤና ጣቢያ ላይ ያለውን መድሃኒት ጭኖ በማሸሽ እና ጤና ኬላውን ማውደም የሚበላ የሚቀመስ እንዳይኖር እህሎችን ማቃጠል ስቃይ ላይ ስቃይ ሲደራረብ ነዋሪዎች ጫካ ገብተው በረሃብና በውሃ ጥም ሲምቱ አንድም የመንግስት አካል የጠየቀ የለም” ሲሉም ከተሰደዱ ሰዎች አንዱ ስለአስከፊነቱ አስረድተዋል።

ይህ ማብቂያ የሌለው የዜይሴዎችን ስቃይ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጭምር ተወካዮቻችን ያስረዱት በመሆኑ የማዕከላዊ መንግስት ቸልተኝነት እስካሁን ትርጉሙ አልገባንም ይላሉ።

ታድያ ሰው ህገመንግስታዊ ጥቃቄ በህጉ የተፃፈውን በመጠየቅ ብቻ ይህ ሁሉ ስቃይና ሞት አይገባም በሀገሪቱ ህግ ካለ ከዚህ ስቃይና የሞት ፅዋ ከመጎንጨት እንዲታደጉን የሀገሬን ህዝቦች እማፀናላሁ ሲሉም የምሬት ሰቆቃን ለሚዲያችን አጋርተዋል።

ስቃይና እንግልት ግድያ ቤት እየሰበሩ በመሸ ቁጥር በጨለማ የሚደርሰው የግድያ ቁጥር ለአይን ለማየት የሚከብድና አጠቃላይ የክልሉ መንግስት ዘይሴዎችን ከምድር ገፅ ለማጥፋት የያዙት የቆየ ሴራ አካል መሆኑን እየደረሰ ካለው ስቃይ ሞትና መከራ መረዳት እንደሚቻል ነፍሳቸውን ለማዳን ወደ ጫካ የገቡት የአከባቢው ነዋሪዎች በውስጥ መስመር መረጃ አድርሰዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ዘይሴዎች ወደ ጫካ እንዲገቡ ያስገደዳቸው ለምን ህገመንግስታዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ጠየቃችሁ በሚል በቀንና በማታ ቤት እየሰበሩ እየገቡ ወጣቱን አዛውንቱን እየደገሉና ወደ ማይታወቅ አከባቢዎች እየወሰዱ ግድያ እንደሚፈፅሙ ከስፍራው አምልጦ የመጣ አንድ ወጣት ስለግድያ በነገረው መረጃ መነሻ ቤት ሆኖ ከመሞት ወጥቶ እየታገሉ መሞትን ምርጫ እንዳደረጉ ስለጉዳዩ አሳሳቢነት አንድ የአካባቢው ሰው በተጨማሪነት መረጃ አድርሶልናል።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media