ለተጎጂዎች ከተሰበሰበው 60 ሚሊዮን ብር ከባንክ ሲያጭበረብር የተያዘው ተጠርጣሪ መሐመድ ኑሩ ሑሴን

በጎፋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለቁበትን መሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ለተጎጂዎች ከተሰበሰበው 60 ሚሊዮን ብር ከባንክ ሲያጭበረብር የተያዘው ተጠርጣሪ መሐመድ ኑሩ ሑሴን "ወንጀሉን ከአስተዳዳሪው ጋር በጋራ ነው የሰራነው!" የሚል ቃል ለመርማሪ ፖሊስና ዓቃቤ ህግ ሰጠ

በጎፋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለቁበትን መሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ለተጎጂዎች ከተሰበሰበው 60 ሚሊዮን ብር ከባንክ ሲያጭበረብር የተያዘው ተጠርጣሪ መሐመድ ኑሩ ሑሴን “ወንጀሉን ከአስተዳዳሪው ጋር በጋራ ነው የሰራነው!” የሚል ቃል ለመርማሪ ፖሊስና ዓቃቤ ህግ ሰጠ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ከአንድ ዓመት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለቁበትን የኬንቾ ሻቻ መሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ፣ ለተጎጂዎች መልሶ ማቋቋሚያ የተሰበሰበውን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ምዝበራን በተመለከተ አስደንጋጭ ተጨማሪ መረጃዎች ወጥተዋል። 

በቼክ ዝውውር ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የሚገኘው አቶ መሐመድ ኑሩ ሑሴን፣ በትናንትናው ዕለት ለጎፋ ዞን ፖሊስና ዓቃቤ ሕግ በሰጠው ቃል፣ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳግማዊ አየለ የዝርፊያው ዋና መሪ መሆናቸውን ማጋለጡን ለ WT Media በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ተደግፎ የደረሰ መረጃ አመልክቷል።

ተጠርጣሪው መሐመድ ኑሩ ሑሴን በቃሉ ላይ እንደገለጸው፦ “የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ዳግማዊ አየለን ከአንድም ሁለት ጊዜ አዲስ አበባ መጥቶ አግኝቼዋለሁ፤ እስካሁን ዝም ያልኩት አላስፈላጊ ዋጋ ላለመክፈል እና ‘አስፈታሃለሁ’ ብሎ ቃል ስለገባልኝ ነው፤ አሁን ግን እውነቱን እናገራለሁ። 

አዎ! ዳግማዊ አየለ እና ምህረቱ ዝናዬ (የአስተዳዳሪው ሚስት ዘመድ) ጋር በጋራ ነው ወንጀሉን የሰራነው!”> ብሏል።

መሐመድ አክሎም ይህ ዝርፊያ የመጀመሪያቸው አለመሆኑንና ከዚህ ቀደምም ከአስተዳዳሪው ጋር መሰል ወንጀሎችን በጥምረት መፈጸማቸውን ለፖሊስ በዝርዝር አስረድቷል።

ተጠርጣሪው ቃሉን በንግግር ብቻ ሳይሆን፣ ወንጀሉ ከመፈጸሙ በፊት ከአስተዳዳሪው ጋር የነበራቸውን ስምምነት የሚያረጋግጡ የድምፅ ቅጂዎች (Voice Records) እና የጽሑፍ መልዕክቶች (SMS) በማስረጃነት ማቅረቡ የታወቀ ሲሆን፣ ይህም በአቶ ዳግማዊ አየለ ላይ የቀረበውን ጥርጣሬ ወደ ማያዳግም ማስረጃነት ቀይሮታል።

መሐመድ ይህንን ሚስጥር ማውጣቱን ተከትሎ፣ በማረሚያ ቤት ውስጥ የግድያ ሙከራ ሊፈጸምበት እንደሚችል ስጋቶች እየተሰሙ ነው። 

ከስፍራው ለ WT Media የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ቃሉን ከሰጠ በኋላ በልዩ ክትትል በአንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ እንዲታሰር ተደርጓል።

 ይህም ሌላኛው “ወንጀሉን የመሸፈን ሙከራ” እንደሆነ ይገመታል።

የዞኑ ፖሊስና የፍትሕ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ፣ የቀረበውን ማስረጃ መነሻ በማድረግ ምርመራ ከመጀመር ይልቅ፣ ጉዳዩ ወደ ገለልተኛ መርማሪ እንዳይሄድና ማስረጃዎች እንዲሰወሩ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

WT Media የዞኑ የፍትሕ መዋቅርና በክልል የሚገኙ የጥቅም ተጋሪ አመራሮች ወንጀሉን ለመሸፈን እየሰራ በመሆኑ፣ ገለልተኛ የፌደራል መርማሪ ቡድን በአስቸኳይ ወደ ስፍራው እንዲላክ፤

እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፦ የቁልፍ ምስክሩ የአቶ መሐመድ ኑሩ ሑሴን ሕይወት እንዲጠበቅ ትኩረት እንዲሰጥና ሕዝቡ ደግሞ ይህንን ግዙፍ ዝርፊያና የፍትሕ መዛባት በንቃት እንድትከታተሉ ጥሪ ያስተላልፋል።

ይህ አሁን በዝርዝር እየተዘገበ ያለው የሙስና ሰንሰለት መነሻው፤ ከወራት በፊት በጎፋ ዞን አደጋ ሥጋት የባንክ አካውንት ላይ የተፈጸመ የ 60 ሚሊዮን ብር ዘረፋ ሙከራ ነው። 

ወንጀሉ የተፈጸመው በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኬንቾ ሻቻ የመሬት መንሸራተት አደጋ አልቀው፣ መላው ዓለም ለተጎጂዎች ዕርዳታ እያፈሰሰ በነበረበት ወቅት ነው።

በወቅቱ አቶ መሐመድ ኑሩ ሑሴን የተባለ ግለሰብ 60 ሚሊዮን ብር የታዘዘበትን የዞኑን የአደጋ ሥጋት ቼክ ይዞ ገንዘቡን ለማውጣት ሲሞክር እጅ ከፈንጂ ተይዞ ነበር።

 ያኔ ጉዳዩ “በግለሰብ ደረጃ የተፈጸመ ስርቆት” ተደርጎ ቢቀርብም፣ የ WT Media የምርመራ ዘገባ ግን ቼኩን የፈረሙትና ወንጀሉን በበላይነት የመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳግማዊ አየለ እንደሆኑ አሁን በወጡ አዳዲስ ማስረጃዎችና በተጠርጣሪው ቃል ተረጋግጧል።

ከዚህ የባንክ ቼክ ዝርፊያ ሙከራ በተጨማሪ፣ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የዓይነትና የጥሬ ገንዘብ እርዳታ የገባበት አለመታወቁ ጉዳዩን የዘመኑ ታላቅ የሰብአዊነት ወንጀል ያደርገዋል።

WT Media በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ በመረጃና በማስረጃ በማስደገፍ በቁርጠኝነት እየዘገበ የቆየ ሲሆን፤ አሁንም አደጋው የደረሰባቸው ወገኖች ፍትሕ እስኪያገኙ እና በሕገ-ወጥ ድርጊቱ የተሳተፉ አካላት በሙሉ ለሕግ ቀርበው ተጠያቂነታቸው እስኪረጋገጥ ድረስ ድምፅ መሆኑን አጠናክሮ ይቀጥላል።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media

1 thought on “የልዩ ምርመራ ዘገባ፦ “ወንጀሉን ከአስተዳዳሪው ጋር በጋራ ነው የሰራነው!” – ለተጎጂዎች ከተሰበሰበው 60 ሚሊዮን ብር ከባንክ ሲያጭበረብር የተያዘው ግለሰብ ለመርማሪ ፖሊስና ዓቃቤ ህግ የሰጠው ቃል”

Comments are closed.