በሀገር ባለውለታ ታዋቂው ተጫዋች የግድያ መዝገብ ነገ የውሳኔ ቀጠሮ አለው

የታዋቂው የባህር ዳር ከተማና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ የግድያ መዝገብ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዎላይታ ምድብ ችሎት ለነገ ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መያዙ ይታወቃል።

ፍርድ ቤቱ ባለፈው መጋቢት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ውሳኔ ለመስጠት ባለመቻሉ ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

 ይህ በተደጋጋሚ የሚሰጥ የቀጠሮ መራዘም በሟች ቤተሰቦች ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ጫና የፈጠረ ሲሆን፣ ከአርባ ምንጭ ወደ ዎላይታ ሶዶ የሚደረገው ተደጋጋሚ ምልልስ ለከፍተኛ እንግልት እንደዳረጋቸው ቤተሰቦቹ ለ WT Media ገልጸዋል።

ቤተሰቦቹ መዝገቡ ከአርባ ምንጭ ወደ ዎላይታ መዛወሩን ክፉኛ እየተቃወሙ ይገኛሉ። 

ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቅሱት በግድያ ወንጀሉ ጥፋተኛ የተባለችው የአደይ ጌታቸው እናት የጎፋ ተወላጅ መሆናቸውን።

የወቅቱ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቦጋለ ፈይሳ የቅርብ ዘመድ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ በፍትሕ ሂደቱ ላይ ተገቢ ያልሆነ ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አሳድረዋል።

 ቤተሰቡ “ይህ በዝምድና ፍትሕን የማጣመም ሴራ ነው” ሲሉ ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

በሐምሌ 2017 ዓ.ም በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሰጠ ውሳኔ፣ ባለቤቱ አደይ ጌታቸው በ16 ዓመት እንዲሁም ሉንጎ ሉቃስ በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ ይታወሳል። አሁን ጉዳዩ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረጃ እየታየ ይገኛል።

WT Media ፍትሕ በዝምድናና በገንዘብ መደለል የለባትም፤ እውነቱ ወጥቶ ፍትሕ ለአለልኝ ሊረጋገጥ ይገባል እያለ ጉዳዩን ነገም በቅርበት መከታተሉን ይቀጥላል።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media